2011-05-06 15:30:31

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሥነ ጽሑፍ እና ድርሰት ለባህል እድገት መሠረት ነው


እ.ኤ.አ. እስከ ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚዘልቀው በሳንቶ ዶሚንጎ እየተካሄደ ወዳለው 14ኛው ዓለም አቀፍ የመጽሐፍት ትርኢት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቃል እና በምስል የተቀረጸ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ። ቅዱስታቸው ባስተላለፉት መልእክት ለሳንቶ ዶሚንጎ ርእሰ ብሔር ሌኦነል ፈርናንደስ እና ለሁሉም እንግዶች እና ተሳታፊዎች ሰላምታን እና ቡራኬ RealAudioMP3 ካቀረቡ በኋላ አክለውም በዚህ መድረክ ቅድስት መንበር ተሳታፊ ብቻ ሳትሆን በሳንቶ ዶሚንጎ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሰበካ ደረጃ የአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት የተጀመረበት 500ኛውን ዓመት ምክንያት በዚህ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍት ትርኢት የክብር ተሳታፊ እንድትሆን በተሰጣት ክብር ምክንያት የተሰማቸው ደስታ በመግለጥ፣ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ አንድ መጽሐፍ መልካም እና ድንቅ የሚያሰኘው ከሚሰጠው ሕንጸት እና ከሚያስተላልፈው ትምህርት ሲለካ ለማሰብ እና ለማስተንተን የሚረዳ ሲሆን ብቻ ነው ያሉትን ሐሳብ በማስታወስ ስለዚህ የአንድ መጽሐፍ መልካምነት መመዘኛው የሚያስተላልፈው መልእክት እና የሚሰጠው ሕንጸት ወሳኝ ነው ብለዋል።

እግዚአብሔር ቃል የሰው ልጅ ቃል በመጠቀም ከእኛ ጋር በመገናኘት እና ያ “ቃል” ሥጋ ሆኖ እንደገና ቃሉ ቃላችን ብቻ ሳይሆን ሥጋው ሰብአዊነታችንን በሙላት ተላብሶ የሰው ደካማ ባህርይ በሙላት የገዛ እራሱ በማድረግ ገዛ እርሱ ወደ ሰዎች በማቅረብ እና የሰው ልጅ ሊረዳው በሚችለው መንገድ በመቅረብ በመንፈስ ቅዱስ አስተንፍሶ አማካኝነት በቃል ከሰው ልጅ ጋር የፈጸመው ግኑኝነት በመጽሐፍ መልክ እርሱም ቅዱስ መጽሐፍ በመሆን የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ለሁሉም ሰው ልጅ እንዲሰበክ፣ የማዳን እቅድ አላማውን አስተዋውቀዋል በማለት ከዚህ በመንደርደር የመጽሐፍ ጥቅም ምን መሆኑ ከገለጡ በኋላ ቅድስት መንበርን ወክለው በዚያ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ትርኢት በመሳተፍ ላይ ለሚገኙት የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚን ሰላምታን እንዳቀረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.