2011-05-06 15:45:46

የቤተ ክርስትያን ተፈጥሮአዊ ተልእኮ የቅዱስ ወንጌልተልእኮ ነው ፡


የ ቤተ ክርስትያን ተፈጥሮአዊ ተልእኮ ሐዋርያዊ ተልእኮ ቅዱስ ወንጌል ነው።

ይህንኑ የገለጡት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲቶስ ናቸው።

ይህንኑ ያላቱም የpapal foundtion የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተቋም አባላት ቫቲካን ውስጥ ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ መሆኑ ቅድስት መንበር የሰጠችው መግለጫ አስታውቀዋል።

ይህ ፓፓል ፋውንደሽን የርእሰ ሊቃነ ጳጳጳሳት ተቋም በጎርግርዮሳዊ አቁጠጣጠር በ1990 በዩናይድ ስቴትስ በብፁዕ ካርዲናል ጆን ክሮል የተመሠረተ ሰብአዊ ተቋም እንደሆነ ይታወቃል።

ተቋሙ ዋነኛ ዓላማ ለችግር የተጋለጡ ሀገረ ስብከቶች የጦርነት እና የርሃብ ሰለባ ለሆኑ ማሕበረ ሰቦች አፋጣን ሰብአዊ ርዳታ የሚሰጥ ተቋም መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ዘግበዋል።

ተቋሙ ለቤተ ክርስትያን ተቋሞች እና ለሰብአዊ ልማት የሚሰጠው እገዛ የሚመስገን መሆኑ ቅድስነታቸው ከተቋሙ አባላት ጋር እንደተገናኙ መግለጣቸው መግለጫው አያይዞ አስገንዝበዋል።

ከዚህ ባሻገርም ለቤተ ክርስትያን ያለውን ሐሳቢነት እና የሰው ሙሉእነት ግሩም መሆኑ ያመለከቱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ተቋሙ በሚያካሄደው ሁለንትናዊ ሰብአዊ እንቅስቃሴ ስኬታማ ይሆን ዘንዳ ያላቸውን ከፍተኛ ተስፋ መግለጣቸውም ተመልክተዋል።

ካቶሊካዊ ተቋሙ በጸጋ እግዚአብሔት የተቀበልነውን ሁሉ ለሌሎች የማስተላለፍ ግዴታችን ገቢራዊ በማደረጉ አኩሪ ተግባር መሆኑ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድተኛ መናገራቸውም ተያይዞ ተገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.