2011-05-05 09:35:39

ቤተ ክርስትያን እና አዳዲስ የመገናኛ ብዙኃን


ቤተ ክርስትያን እና አዳዲስ የመገናኛ ብዙሃን በሚል ርእስ ሥር ለየት ባለ መልኩ በድረ ገጾች በኵል ሰዎች ወይንም ማኅበራት እና ማኅበረሰብ በየዕለቱ የሚያቀርቡት እርሱም በተለያየ ርእሰ ጉዳይ ላይ በማተኮር ርእሰ ጉዳዩንም በተለያየ ዘርፍ በመመልከት የሚሰጡበት ትንታኔ እና የማስረጃ ዜና መዋዕል ላይ በማተኮር የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በጋራ ያዘጋጁት ዓውደ ጥናት ከትላትና በስትያ እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በቫቲካን እየተካሄደ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ በመካሄድ ላይ ስላለው ዓውደ ጥናት በማስመልከት የባህል ጉዳይ በሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የግኑኝነት እና የሥነ ቋንቋ ጉዳይ የሚመለከት ቢሮ ተጠሪ የዓውደ ጥናቱ ደራሲ ዶክተር ሪቻርድ ሩሰ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ወቅታዊው ባህል የዜና መዋዕል ድረ ገጾች መስፋፋት የሚታይበት የተለያዩ ሰብአዊ ፖለቲካዊ ባህላዊ ፍልስፍናዊ ቲዮሎጊያዊ ባጠቃላይ በተለያዩ የምርምር እና የጥናት ዘርፎች አማካኝነት የሚነሱት ዓበይት እና አንገብጋቢ ጥያቄዎች ላይ በማተኮር የሚዘረዘሩት መልሶች እና የትንተና ዜና መዋዕል ላይ በማነጣጠር የዚህ አዲስ የድረ ገጽ ዜና መዋዕል ዓላማው ምን መሆኑ ለማወቅ፣ የዜና መዋዕል ደረ ገጾች አማንያን ኢአማንያን የዜና መዋዕል ድረ ገጽ ደራሲያን የሚሳተፉበት ዓውደ ጥናት መሆኑ ሲገለጡ፣ አንድ ቋንቋ ተገልጋዩን ሰው ይለውጣል ይገልጣልም ሲሉ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ያሉትን ሃሳብ በማስታወስ፣ ቤተ ክርስትያን በዚህ በሥን አኃዝ በተራቀቀው ዓለም ለምታቀርበው አስፍሆተ ወንጌል እና ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አቢይ ድጋፍ አለው ብለዋል።

ይህ አዲሱ የዜና መዋዕል ድረ ገጾች በኵሉ የውይይት ባህል ለማነቃቃት አማኙ ለአማኙ ብቻ ሳይሆን ከኢአማንያን ጋር የሚወያይበት ኅብረ ባህል የሚያጎላ፣ እያንዳንዱ ማኅበራዊ ድረ ገጽ በሚያተኩርበት ርእሰ ጉዳይ መሠረት የተዘጋ ሳይሆን በሚያተኩርበት ርእሰ ጉዳይ በኩል ከሁሉም ጋር የሚወያይ ክፍት መሆን አለበት፣ ስለዚህ ድረ ገጻዊ መለያው የሚያገል፣ ሌላውን የሚነጥል መሆን የለበትም ከሚለው አመለካከት በመንደርደር በተዘጋጀው ዓውደ ጥናት 150 የዜና መዋዕል ድረ ገጾች ዋና አዘጋጆች እያተሳተፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ ቤተ ክርስትያን በዚህ አዲስ በሥነ አኃዝ በተራቀቀው መሣሪያ በኵል የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮዋ እያከናወነች መሆኗ ገልጠው፣ የተጀመረው አወደ ጥናት በዚህ የሚጠቃለል ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መርሃ ግብር መሠረት በተለያዩ ጊዚያት እንደሚካሄድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አረጋግጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.