2011-05-05 09:38:09

በቪኪ ዘመን ይመለክ የነበረው ቶር የነጎድጓድ ጣዖት ታሪክ


የኖረና የሥነ ጥንት ታሪክ እንደሚገልጠው፣ በሰሜን ኤውሮጳ የሥነ ጥንተ ታሪክ በዚህ የኤውሮጳ ክልል ይመለኩ ከነበሩት ጣዖቶች ውስጥ አንዱ ቶር በሚል መጠሪያ የሚታወቅ የኖጎድጓድ አምላክ ተብሎ የሚነገርለት ይመለከቱ ከነበሩት ጣዖቶች ውስጥ አንዱ መሆኑ የኖረና የሥነ ጥንት ታሪክ የሚገልጠውም ሲሆን፣ ይኸንን ያልተገለጠ ሃይማኖት በታሪክ መሠረት የተላለፈ ባህል ሳይሆን፣ በቃል ከትውልድ ወደ ትውልድ የተወራረሰ የመጣ መሆኑ የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ታሪክ ያረጋግጠዋል። ስለዚህ የኖረና የሥነ ጥንት ታሪክ በተመለከተ የጽሑፍ ታሪካዊ መረጃው በዚህ የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ታሪክ የኤዳ ሁለቱ ምዕራፎች ላይ ተመልክቶ የሚገኝ ሲሆን፣ የኖረና የሥነ ጥንት ታሪክ ለተለያዩ የትያትር የፊልም እና የሥነ ጽሑፍ ድርሰቶች ምንጭ በመሆን የሚያገልግል መሆኑም ለማወቅ ሲቻል፣ ይከንን መሠረት በማድረግ የሼክስፒር የትያትር ድርሰቶች ሊቅ አቢይ ሸኪስፒራዊ ተወናያን ኬንዝ ብራንጋህ የደረሱት ትያትር ለትርኢት ይቀርባል።

ይኽ ቶር የቪኪ ጣዖታዊው የነጎድጓድ አምላክ ታሪክ ከመጽሓፍ ቅዱስ ጋር በማመሳሰል፣ ቶር ቅናት የሥልጣን ሽኩቻ፣ ትዕቢት የመሳሰሉት የሰውን ልጅ ልብ የሚያደነድኑ በሰው ልጅ መካከል መከፋፈል እና ጭቆናን የሚያስከትሉ እንዲሁም አስመሳይነት እና አድር ባይነት የሥልጣን ግትርነት እና አምባገነናዊ መልኩን በመጻረር ባጠቃላይ ይኸንን የሰው ልጅ ደመ ነፍሳዊ ዝንባሌ ያለው ባህርይ ለማጥፋት የሚፈጽመው ትግል የሚያወሳ ትያትር መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሂዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ የሰው ልጅ በመንግሥተ ሰማያት ከመንግስተ ሰማይ መባረር ከቃኤል እና አቤል ታሪክ ጋር የሚመሳሰል የመጽሓፍ ቅዱስ ታሪክ የሚያጎላው ገጽታውን በመለየት ለትርኢት ለማቅረብ አቅደው በጥልቅ የቶር ሥነ ጥንታዊው ጥናት በማጥናት የደረሱት ትያትር መሆኑ በመግለጥ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.