2011-05-04 17:25:19

‘ጌታ ሆይ! ጸሎት ኣስተምረን’ (ሉቃ 11፡11)


የር.ሊ.ጳ ሳምትንታዊ የዕለተ ሮብ ኣጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (04.05.11)፤ ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ ዛሬ ኣዲስ የትምህርተ ክርስቶስ ዙርያ ለመጀመር እወዳለሁ። ስለ በመሃከለኛው ዘመን የነበሩ የቤተ ክርስትያን ኣበው ትላልቅ የትምህርተ ንባበ መለኮት ሊቃውንት ትላልቅ ቅዱሳን ሴቶች ረዘም ላለ ግዜ ካስተማርን በኋላ በእያንዳንዳችል ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ስላለው ስለጸሎት በተለይም ስለ ክርስትያን ጸሎት መናገር እወዳለሁ፤ ይህ ጸሎት ጌታ ያስታማረን ጸሎት ሲሆን ቤተ ክርስትያን ደግሞ እርሱ ዳግም እስኪመጣ ድረስ ታስተምረናለች። እንደ እውነቱ ከሆነ የሰው ልጅ በጥልቀትና በጓደኝነት ወደ እግዚአብሔር በወላጅና ልጅ ግኑኝነት ሊጠጋ የሚችለው በኢየሱስ ብቻ ነው። ከመጀመርያዎቹ ኣርድ እት ጋር በመሆን ትሕትና በተላበሰ መተማመን ‘ጌታ ሆይ፤ ጸሎት ኣስተምረን’ ብለን እንጠይቀው።

በሚቀጥለው የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮዎች በቅዱስ መጽሓፍ በቤተ ክርስትያን ኣበው ትውፊት በመንፈሳውነት ኣስተማሪዎች እና በሥርዓተ ኣምልኮ በመመርኮስና በመጠጋት ከጌታ ጋር ጥብቅ በሆነ ግኑኝነት እንድንኖር ስለጸሎት እንማራለን፤ የጸሎት ትምህርት ቤት ዓይነት እንደ ማለት ነው። ጸሎት እንዲያው የሚገኝ ማንም ነገር እንዳልሆነ ሁላችን እናውቃለን፤ ዘወትር ይህንን ጥበብ በታደሰ መልኩ እየተጠቀምን ጸሎት ማድረግ መማር ኣለብን፤ በመንፈሳውነት በጣም ዘልቀው ያለው መንፈሳውያን ሰዎች ሳይቀሩ ጸሎትን በብቃት እንዲወጡት ዘወትር በኢየሱስ ትምህርት ቤት እየተማሩት ነው።

የጸሎት መጀመርያ ትምህርት ከኢየሱስ ኣብነት እናገኘዋለን። ወንጌላውያን ኢየሱስ ዘወትር በጸሎት ከኣባቱ ጋር ጥልቅ ግኑኝነት እንደነበረው ይገልጡልናል። ይህ ግኑኝነት የገዛ ራሱን ፈቃድ ሳይሆን የሰው ልጅን ለመዳን የላከው የኣባቱን ፈቃድ ለመፈጸም በዚህ ዓለም የመጣ ኢየሱስና የኣባቱ ጥልቅ ኣንድነትን ያመለክታል።

በዚሁ የመጀመርያ ትምህርተ ክርስቶስ እንደ መግቢያ እንዲሆንልን በጥንታዊ ባህሎች የነበሩትን የጸሎት ኣብነቶች መጥቀስ እውዳለሁ። እነኚህ ጸሎቶች የሚያስተምሩን ተግባራዊ በሆነ ቀለል ባለ መንገድ እንዴት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እንደሚቻል ነው።

እንደ ኣብነት በጥንታዊትዋ ግብጽ እጀምራለሁ፤ በዚሁ ኣገር ኣንድ ዓይነ ሥውር መላእክቱ ኣይኖቹን እንዲከፍቱለት ይለምናል፤ ማንኛው ሰው በዓለም እንደሚያደርገውም በተስፋ ይጠባበቃል። ይህ መጠባበቅ ንጹሕና ገር የሆነ ጸሎት ሆኖ በችግር የሚገኝ የሚያቀርበው ጥያቄ ነው። ዓይነ ሥውሩ ሰውየ ‘ጨለማን ለማየት የፈጠርከኝ፤ ልቤ እንዲያይህ ይፈልጋልና ብርሃን ፍጠርልኝ። እኔ እንዳይህ ዘንድ ክቡር ፊትህን ወደኔ ኣቅና’ ይላል፤ የጸሎቱ ኣንኳር እኔ ለማየት እንድችል የሚለው ነው።

በጥንታዊው መሶጳጣምያ የጋራ የሆነ ኣደንዛዥ የጥፋት ስሜት ይገዛ ነበር፤ ሆኖም ግን ተስፋ የሚያስቆርጥ ግን ኣልነበረም፤ በእግዚአብሔር መካካስ ነጻነት ይመጣል የሚል ተስፋ ነበራቸው። እነዚህ ጥንታውያን ኣማንያን ከሚያሳርጉት ጸሎት ይህንን መጥቀስ እንችላለን፤ ‘ኦ እግዚአብሔር ትልቅ ጥፋት ሳይቀር ትምራለህ፤ ከኃጢኣቴ ኣንጻኝ፤ ባርያህን ተመልከት የደህንነት እስትንፋስህን በእርሱ ላይ ኣስተንፍስ፤ ሳትቀየምና በደሉን ሳትቆጥር ማረው፤ ካስፈሪው ቅጣትህ ኣውጣው፤ ሕይወት ኣግኝቼ ለማስተንፈስ እንድችል ዘንድ፤ኣስሮኝ ያለውን ሰንሰለት በጣጥሰህ ፍታኝ’ ይላል።

እነኚህ ጸሎቶች የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ሲፈልግ ተፈጥሮ ባደለው ሓሳብ ያልተነጣጠረም ቢሆን እንዴት ኣድርጎ ባንድ በሁል በደሉን በሌላ በኩል ደግሞ የመለኮታዊ ኃይሉ ምሕረትና ርኅራኄን ያመለክታሉ።

በጥንታዊትዋ ኣረሜን ግሪክ እምነት ውስጥ ለጸሎት በጣም ጥሩ ትርጓሜ የሚሰጥ ዕድገት ይታይ ነበር። እነኚህ ሰዎች ሲጸልዩ በሁሉም ዕለታዊ ሁኔታዎቻቸው እርዳታ እንዲደርጋልቸውና የሚያስፈልጋቸውን እንዲያገኙ ሰማያዊ ደገፍና እርዳታ ቢለምኑም ቅሉ ልክ እኛ ኣማንያን እንድምንለምነው ሁሉ እሳቸውም ከሰማያዊው ጋር የላቀ ግኑኝነት እንዲኖራቸውና በኣኗኗራቸው ሕይወታቸው ወደ መልካም ነገር እንዲያዳላ ይለምኑ ነበር። ለምሳሌ ትልቁ ፍላስፋ ፕላቶ የኣስተማሪውና የምዕራባዊ ፍልስፍና ኣባት የሆነው የሶቅራጥስ ጸሎት ጽፎ እናገኛለን፤ ሶቅራጥስ እንዲህ ብሎ ይጸልይ ነበር፤ ‘ጌታ ሆይ እኔ በውስጤ መልካም እንዲሆን ኣድርገኝ፤ ሃብታም የምቆጥረው ባለገንዘብን ሳይሆን ጥበበኛን እንዲሆን ከገንዘብም ጥበበኛ ሊኖረውና ሊይዘው የሚችለውን ያህል እንዲኖረኝ ኣድርግ፤ ከዚህ ሌላ ምንም ነገር ኣለምንህም’። ከሁሉም ይልቅ ውሳጣዊ ቁንጅናና ጥበብን ይፈልግ ነበር እንጂ በገንዘብ ባለጠጋ መሆንን ኣይደለም።

የሁሉም ዘመናት ትላልቅ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች የግሪክ ትራጀዲዎች የተመለከትን እንደሆነ ዛሬም ከ25 ክፍለዘመናት በኋላ ለንባብና ኣስተንትኖ ተወዳጅ ከመሆናቸው ባሻገር እግዚአብሔር ለማወቅ የሚደረግ ጸሎትና የእርሱን ግርማዊነት ለማክበር የነበረ ፍላጎቶችን ይዘው ይገኛሉ። ለምሳሌ ‘የምድር ደጋፊ ከምድር በላይ የምትኖር ልንረዳህ የማንችል የሆንክ ሁን ዘውስ፤ የተፈጥሮ ሕግ ኣንተ ነህ፤ የመዋቾች የሐሳብ ምንጭም ኣንተ ነህ፤ የሰው ልጅ ሁኔታን በፍትህ መሠረት የምትመራ ኣንተ ስለሆንክ፤ በጽሞና ባንተ እማጠናለሁ’ የሚል ጸሎት እናገኛለን። እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ነገር ያልተነጠረ ደብዘዝ ያለ ሐሳብ ቢሆንም የሰው ልጅ ይህንን ያልታወቀውን እግዚአብሔር ለማወቅ እንዲችልና የምድር መንገዶች እንዲመራላቸው እንደሚጸልዩ እንመለከታለን።

የጥንት ሮማዊያን መግንሥት እንኳ በታላቅነታቸውና በግዛታቸው የታወቁ ቢሆኑ የክርስትናን እምነት የተወለደበትና መሠረት በመጣል አብሮ ከጸሎት ጋር የዳበረ ሲሆን፡ ጸሎት ጠቃሚና አስፈላጊነቱ የአምላካቸውን ጥበቃና በሕይወታቸውና ለሚኖሩበት ኅብረተሰብ በጸሎት ጥያቄ ሲያቀርቡና ከዚያም ባሻገር ከምስጋና ሌላ ምሕረትን ሲማልዱ፤ ንስሐን ይቅርታ ሲለምኑ ያም ወደ ውዳሴና ምስጋና ተሞልቶ ፈጣሪያቸውን ሲያመሰግኑ በታሪክ ተጽፎ እናገኛለን።

ለዚህ ታሪክ ምስክር ከክርስቶስ ሞት በ2ኛው ክፍለ ዘመን ላይ የነበረው የአፍሪካው ሮማን ጸሐፊ አፑሌዮ በደረሰው መጽሃፍ ላይ እንመለከታለን።

በአፑሌዮ ጽሑፎች ላይ ያኔ እንዳሁኑ በባህል ሃይማኖት የነበራቸው እምነት እንደማያረካቸና ነገር ግን ምኞታቸው ከፈጣሪያቸው ጋር ቀጥተኛና እውነተኛ ግንኙነት እንዲኖራቸው መፈለጋቸው እንመለከታለን።

አፑሌዮ ከጻፋቸው ጽሑፎች አንዱ በጣም የሚታወቀው le metamorfosi (መሰረታዊ ለውጥ)

የተባለው መጽሓፉ ላይ ምንም እንኳ ፈጣሪያቸውን በቀጥታ ባያውቁትም ነገር ግን አንድ አማኝ ለአንዲት ሴት ፈጣሪ ጸሎቱን ሲያቀርብ አንቺ ጻድቅ ነሽ፡ በማንኛውም ግዜና ቦታ የሰውን ነፍስ የምታድኝ፡ ልግስናሽ ብዙ፡ ለኛ መዋች ሰዎች እርዳታን የምታደርጊ፡ ለተቸገሩና ለተጎዱ ሰዎች የእናትነት ፍቅር የምትሰጭ፡ ቀንም ለሊትም ደቂቃም ሰከንድም ለጥቂትም ቢሆን አንቺን የለመነ ሳይጠቀም ያለፈ የለም። በማለት ይጸልዩ ነበር።

በዛን ዘመን የሮማው ንጉሥ ማርኮ አውሬልዮ የፍልስፍና ምሁር እንደነበር ቢታወቅም በተለይም ለሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኘው ጸሎት ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል። በሱ ማስታወሻ መጽሓፍ ላይ “በእኛ ውሳኔ ማድረግ ላለብን የሰማይ አማልክት አይረዱንም ያለ ማን ነው?

በመጀመሪያ መጸለይ ጀምርና ውጤቱንም ታያለህ” ብሎ ጽፈዋል።

የጥንቱ ፈላስፋ የሮማ ንጉሥ ማርክ አውሬሊዮ ምክር ከክርስቶስ ልደት በፊትም ቢሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ያለውን ሽግግር ስንመለከትና የሰው ልጅም ያለ ጸሎት እንዳልኖረ፤ ይህም የኛ መሠረታችን ከእግዚአብሔር ምሥጢር ጋር ሲያያዝ መሆኑ፤ ኣለበለዚያ ግን ሕይወታችን የሕይወት ትርጉም የለውም።

በማንኛውም ጸሎት ላይ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ሁኔታ ሲገለጥ፤ ይህም ባንድ በኩል ድክመቱንና ችግሩን ከሰማይ እርዳታን በመጠየቅ ሲጸልይ በሌላ በኩል ደግሞ ክብሩን ሲገልጽ፤ ይህም የአምላኩን መገለጥ፡ ከእርሱ ጋር ውስጣዊ ግንኙነት በመፍጠር የሚገለጥለት ክብሩን ያሳያል።

የተከበራችሁ ጓደኞቼ በተመለከትናቸው የተለያዩ ዘመናትና ሥልጣኔዎች የጸሎት ኣብነቶች የሰው ልጅ ፍጡር መሆኑና ባንድ ከእርሱ በላይ በሆነ እንዲሁም የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ በሆነ እንደሚጠጋ ማወቁ ጐልቶ ይታያል። የሁሉ ዘመናት ሰው ከምሥጢረ እግዚአብሔርና እሱ ለዓለማችን ካቀደው መደብ ጋር ካላገናኘው ሁል ግዜ ደብዛዛና ኣስቸጋሪ የሆነው የሕይወቱ ትርጉም ለማወቅ ጸሎት ሲያሳርግ ኖረዋል። የሰው ልጅ ሕይወት በመጥፎ ነገርና በበጎ ነገር እንዲሁም በማይረዳው ሥቃይ በደስታና በቁንጅና የተወሳሰበ ነው። ይህ ሁኔታም በደመ ነፍስ ተመርተን በዚህ ምድር ሊረዱን የሚችሉና ከሞት ባሻገር ተስፋ የሚሰጡ ውሳጣዊ ብርሃንና ኃይል እግዚአብሔር እንዲሰጠን ለመለምን እንገደዳለን።

ኣረማውያን ሃይማኖቶች ከሰማይ ቃል በመጠባበቅ ከዚህ ምድር የሚቀርቡ ልመናዎች ናቸው። ከመጨርሻዎቹ ትላልቅ ኣረማውያን ፍላስፋዎች ኣንዱ የሆነው በክርስትና ዘመናችን የኖረው ፕሮኮሎ ዘቁስጥንጥንያ ለዚህ የሚሆን ምስክርነት ይሰጣል። ‘የማትታወቅ ኣምላካችን፡ የሚይዝህ የለም፤ የምናስበው ሁሉ ያንተ ነው፤ የእኛ መልካም ነገሮችና መጥፎ ነገሮች ካንተ ናቸው፤ ሁኔታችን ሁሉ ባንተ ይጠጋል፤ የሰው ኅሊና ሊደርስህ የማይቻለው ጌታ ሆይ ነፍሶቻችን የዝምታ ማኅሌት እያሳርጉ መኖርህን ያጣጥማሉ’ ብሎ መጸለዩን ጽሑፎቹ ያመልክታሉ።

እንደኣብነት ባቀረብናቸው የተለያዩ ባህሎች ጸሎቶች በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ልብ ውስጥ የሃይማኖት ዝንባሌና የእግዚኣብሔር ፍላጎት ተጽፎ እንዳለ ለማረጋገጥ ችለናል፤ እነኚህ ሁኔታዎች በቅዱስ መጽሓፍ በብሉይና በኣዲስ ኪዳን ፍጽምና ያገኛሉ። የእግዚአብሔር ግልጸት ይህንን በሰው ልብ ያለውን ጥንተ ነገራዊ ፍላጎት በጸሎት መንገድ ከሰማያዊ ኣባቱ ጋር ጥልቅ ግኑኝነት ለማድረግ ዕድል በመስጠት ያነጸዋል፡ ፍጽምናም ይሰጠዋል።

ዛሬ በምንጀምረው የጸሎት ትምህርት ቤት ጉዞ እንደገና ጌታ በጸሎት ከእርሱ ጋር የምናደርገው ግኑኝነት በጋለ ስሜት በፍቅርና በማያቋርጥ መንገድ እንድናድርገው ዘንድ ልባችንና ኣእምሮኣችን እንዲያበራልን እንለምነው፤ እንደግና “ጌታ ሆይ! ጸሎት ኣስተምረን’ ብለን እንጠይቀው።








All the contents on this site are copyrighted ©.