2011-04-18 15:33:20

የበዓለ ሆሣዕና ሊጡርጊያ ምንባበ ወንጌል ትንታኔ በቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ሰኮንዲኒ


በትላትናው የበዓለ ሆሣዕና ሊጡርጊያ ምንባበ ወንጌል መሠረት የተነበበው የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ እና ህማማት ይኽ ደግሞ ከይሁዳ ክህደት እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቀበር የሚያወሳ እና ከእኩለ ቀን RealAudioMP3 እስከ ስለስቱ ሰዓት ያለው ምድር በጨለማ እና ድንቅድ ባለ ባዶነት የተዋጠችበት ተጨባጭ ሁኔታ የሚያወሳ፣ አባቴ ሆይ ለምን ተውከኝ በሚለው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድምጸ ቃላት ተመልክቶ የሚገኝ መሆኑ የቀርመሊዮስ ገዳማውያን ማህበር አባል በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የሥነ መንፈሳዊ ቲዮሎጊያ መምህር የቲዮሎጊያ እና የመጽሓፍ ቅዱስ ሊቅ አባ ብሩኖ ሰኮንዲኒ በራዲዮ ቫቲካን በኩል ባቀረቡት አስተንትኖ ገልጠው፣ ይህ ሳምንት ወደ የሕማማት ሳምንት የምንገባበት በማቴዎስ ወንጌል ባለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቃይ እና የሕማማት ንባብ መሠረት የተተረከው እውነተኛው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ ታሪክ ስናዳምጥ ልባችን በሐዘን ይነካል። ብዙዎቻችን እግዚአብሔር እንዴት አንድ ልጁን ከሞት አያድንም? ለምን በመስቀል ላይ ውሎ መራራ ብቸኝነት ለማለፍ እና የተናቀ እስከ መሆን በቃ? የተሰኙት ጥያቄዎች አቅርበው፣ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ በእምነት ምሥጢር ማለፍ ግድ ነው። ስቁል ኢየሱስ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እራስን አሳልፎ እስከ መስጠት ምንኛ እንዳፈቀረን በተጨባጭ ሁኔታ ይገልጥልናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቱ እስከ ሞት ድረስ ያሳየው ተአዝዞ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለው ፍጹም እና ሙሉ ታማኝነት ምልክት ነው። ይኽ ደግሞ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይጠብቁ የነበሩት ኢአማኒያን ወታደሮች ቀርበው ያረጋገጡት እውነት ነው።

እንዲህ ያለ ፍጹም ፍቅር እግዚአብሔር ብቻ ነው ለመኖር እና ለመፈጸም የሚችለው፣ እንዲህ ያለ ታሪክ መረጃው እና ፍቹም እግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ጳውሎስ ወደ ገላትያ ሰዎች በጻፈው መልእክት ምዕራፍ 3 ቁጥር 13 “በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የሚሞት ሁሉ የተረገመ ነው። ተብሎ ስለተጻፈ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን” ሲል መስክሮታል። ስቁል እየሱስ የፍጹም ፍቅር ኃይለኛነት ምልክት ነው። ስለዚህ መስቀሉን እናምልከው እናፍቅረው በማለት የያቀረቡት ያስተንትኖ ስብከት ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.