2011-04-18 15:30:31

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ አጭር የትምህርተ ክርስቶስ ሰነድ ትልቅ የእምነት መልስ


ዩካት በሚል መጠሪያ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ለካቶሊክ ወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ ደግፊ ሰነድ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመግቢያ ጽሑፍ ያስቀደመ 300 ገጽ አዘል የወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ መጽሓፍ በቅርቡ ለንባብ እንደሚቀርብ ሲገለጥ። ይህ ጥያቄ እና መልስ በማስከተል የተደረሰ የክርስትና እምነት ለማወቅ የሚያግዝ እና የክርስትና እምነት መለያ የሚያሳወቅ RealAudioMP3 መጽሓፍ እ.ኤ.አ. ነሓሴ ወር በማድሪድ ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አቢይ ድጋፍ ይሆን ዘንድ ታስቦ በሰባት ቋንቋዎች ታትሞ እንደሚቀርብ እና ለእያንዳንዱ 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊ ወጣት የሚሰጥ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቅዳሜ ባቀረቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቅጽ በማብራራት፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሃይማኖት ትምህርት እና በዓንቀጸ ሃይማኖት በቤት ክርስትያን ትውፊት ላይ በጸና የእምነት ትምህርት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ወጣት ምእመን እንዲታነጽ የሚይግዝ የወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ መሆኑ ከርእሰ ዓንቀጹ ለመረዳት ተችለዋል።

በር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልዩ ፍላጎት መሠረት የካቶሊክ ትምህርተ ሃይማኖት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ርራትዚንገር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ልዩ ክትትል ለፍጻሜ የበቃው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ሥልት የተከተለ እና መሠረት ያደረገ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አብራርተው፣ ካቶሊክ ማኅበረ ክርስትያን በእምነት ትምህርት ጉዞ ሳይደናገር በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሥር ውህደት እንዲኖረው የሚያግዝ ጭምር ነው ብለዋል።

የካቶሊክ እምነት የሚማርክ ልብን እና አእምሮን የሚናገር ሆኖ ለወጣቱ ለማቅረብ እና ወጣቱ በዕለታዊ ኑሮው ለሚያቀርባቸው አበይት እና አንገብጋቢ የኅልውና ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ሆኖ የተዘጋጀ ነው። እምነት እንዲህ ባለ መልኩ ካልተላለፈ ወጣቱ ቀስ በቀስ ከእምነት እየራቀ ነው የሚሄደው። ከወጣቶች ጋር በመሆን ትልቁን ትምህርተ ክርስቶስ መቋደስ አብሮ ማጥናት በጥልቅ ለመረዳት ጥረት ማድረግ እና መጸለይ፣ ከዚህ ባሻገር ለሌሎች ማቅረብ እና ምስክርነት የሚጠይቅ የእምነት መሣሪያ ነው ብለዋል።

ይኽ ዩካት የተሰየመው የካቶሊክ ወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ መጽሐፍ ፍጹም ሳይሆን ዕለት በዕለት በትምህርተ ሃይማኖት ደረጃ ሳይሆን በቃላት አጠቃቀም እና አሰካክ የሚጠና እየተሻሻለ የሚሄድ ነው። ለወጣቱ ትውልድ የደስታ መንገድ የሚያመለክት የመልካም እምነት ጉዞ መጽሓፍ ነው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.