2011-04-18 15:29:10

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ እውነተኛ ነጻነት የሚሰጠን እና ነጻ የሚያወጣን ዕደ ጥበባዊ እድገት ሳይሆን የእግዚአብሔር ፍቅር ነው።


ትላትና እሁድ የላቲን ሥርዓት ግጻዌ የምክትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በዓለ ሆሣዕና አክበራ ውላለች። እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ከዚሁ ዓቢይ በዓል ጋር በማያያዝ የኢጣሊያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብሔራዊ የወጣቶች ቀን የምታከብርበት ዕለት እና ሁሌ በኩላዊት ቤተ ክርስትያን አነሳሽነት በየዓመቱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመገኘት አስተምህሮ እና መሪ ቃል የሚለግሱበት በዓለም አቀፍ RealAudioMP3 ደረጃ ለሚከበረው የወጣቶች የሚሸኝ በመሆኑም ምክንያት፣ ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ከ ነሐሴ 16 ቀን እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ እና ፈቃድ መሠረት በማድሪድ ለሚከበረው 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማዘጋጃ ጭምሮ ሆኖ መታሰቡም ለማወቅ ተችለዋል።

በዓለ ሆሣዕና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕዝብ የሞቀ ድጋፍ እና ጭብጨባ ተሸኝቶ ንጉሣዊ ሥልጣኑ እውቅና አግኝቶ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ቀን የሚከበርበት ዕለት ሲሆን፣ ሆኖም ግን ንጉሥ በማለት ንግሥናው እውቅና የሰጠው ሕዝብ ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ለሞት ተላልፎ እንዲሰጥ ድምጹን በከፍተኛ ጩኸት ያሰማል። የዘንባባ ቅርንጫፍ በመስቀል ተተክቶ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ተሸክሞ በእግዚአብሔር እና በሰው ልጅ መካከል ተዘግቶ የነበረውን በር እንዲከፈት ማድረጉ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. 2007 ዓ.ም. በሆሣዕና በዓል ምክንያት ባሰሙት ስብከት በመግለጥ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ዘወትር ለእግዚአብሔር የተዘጉ የዓለም በሮች እና የእያንዳንዱ የሰውን ልጅ የልብ በር በማንኳኳት እግዚአብሔር በመፍጠር ኅላዌውን በመስጠት ሁሉን ንገር ኅያው ከማድረግም አልፎ በእርሱ ለማመን ይህ አልበቃኝም ብሎም ቃሉም ከቤተ ክርስትያን ለሚቀርበው ጥሪ ችላ ለሚለው መላው የሰው ዘር ገዛ እራሱን ለእግዚአብሔር ክፍት እንዲያደርግ የሰውን ልጅ ስቃይ ስለ ፍቅር ብሎ በመቀበል እና የራሱን በማድረግ ተሰቃየ።

የእግዚአብሔር ፈቃድ ከእኛ ፈቃድ ይልቅ ዘወትር አስፈላጊ እና እውነተኛ መሆኑ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ለበዓለ ሆሣዕና ባሰሙት ስብከት በማብራራት፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ እውነት እና ፍቅር ነው እንዳሉ የቅዱስ መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

ሁሌ በየዓመቱ በሆሣዕና በዓል በኢጣሊያ ብሔራው የወጣቶች ቀን የሚክበርበት ዕለት በመሆኑም ምክንያት እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 16 ቀን እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በቤተ ክርስትያን ውሳኔ መሠረት በማድሪድ የቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ለቆላስያስ ሰዎች የጻፈው መልእክት ምዕራፍ 2 ቁጥር 7 “በእርሱ ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ በተማራችሁት መሠረት በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ፣ ብዙም አመስግኑ።” በሚል ቃል ተመርቶ የሚከበረው ለ 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ባስተላለፉት መልእክት፣ የሚያምን ያማያምን ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል የዚህ የሞተው ሞትን አሸንፎ የተነሣው ኅያው የሆነው የጌታችን ፍቅር ሁሉም እያንዳንዳችን የሕይወታችን ተመክሮ ለማድረግ እንችላለን። የሚያምን ይኸንን ፍቅር በቃል እና በሕይወት በመመስከር የክርስትና ተስፋ ለዓለም ሁሉ ለማሳወቅ የፍቅር ኃላፊነት አለበት ሲሉ ማብራራታቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ትላትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በላቲን ሥርዓት ግጻዌ መሠረት ለበዓለ ሆሣዕና ከውጭ እና ከአገር ውስጥ የመጡት ነጋድያን የኢጣሊያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብሔራዊ የውጣቶች ቀን ምክንያት ከሁሉም ሰበካዎች እና ቁምስናዎች የተወጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት ከ 50 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ምእመናን ዘንባባ ቅርንጫፍ በማውለብለብ በቅዱስ አባታችን የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ብፁዓን ካርዲላኖች ተመርቶ በተካሄደው ዑደት ቅዱስነታቸው ተሳትፈው ዑደት እንዳበቃም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፣ በዓለ ሆሣዕና ከግብጽ ባርነት ነጻ የተወጣበት ፍጹም እና እውነተኛው የተስፋ ምልክት ወደ ሆነው በዓለ ፋሲካ የሚሸኝ ዓቢይ በዓል ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበጉ ደመ ምሥዋዕት በገዛ እራሱ ደም በመተካት እራሱን በመስቀል አሳልፎ የሚሰጥበት አዲስ ፋሲካ መሆኑ ያውቃል። በዚህ የሆሣዕና በዓል የሚደረገው መንፈሳዊ ዑደት ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በመሆን ወደ ኅያው እግዚአብሔር የሚወስደው በላቀው መንገድ የምንጓዝ ለመሆናችን ምልክት ነው። ይኽ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልንከተለው የሚገባንን በገለጠው መንገድ የምንራመድ መሆናችን የምንመሰክርበት ዕለት ነው ብለዋል።

ሆኖም በዚህ ጉዞ ወደ ታች እንድናሽቆለቁል የሚስበን ኃይል ቀላል አይደለም፣ በእኛ ብቃት አማክኝነት መልካምነት ብቻ ሳይሆን ሊከሰት የሚችለው ክፋት ጭምር ተነቃቅተዋል። የክፋት እምቁ ኃይል ከፍ እያለ በታሪክ ላይ የሚዝት ማዕበል ሆኖ ይጋረጣል። የሰው ልጅ ውሱንነት አሁንም እንዳለ ነው። ለዚህ ማረጋገጫም በቅርቡ የተከሰተው ጉዳት ያስከተለው ስቃይ እና ገና የሰው ልጅ እያሰቃየ ያለው እልቂት ማስታወሱ በቂ ነው።

የሰው ልጅ በነዚህ ሁለት ስበት መካከል ተወጥሮ እንደሚገኝ ገልጠው፣ ከክፋቱ ስበት ለማምለጥ እና ነጻ ለመሆን በእግዚአብሔር ስበት ይማረክ እና ይሳብም ዘንድ የሰው ልጅ ገዛ እራሱ ሊፈቅድ እና እሺ ማለት ይጠበቅበታል።

የተጨበጡት አበይት ዕደ ጥበባውያን ክንዋኔዎች እና እድገቶች ለሰው ልጅ እድግት እና ብልጽግና ደጋፊ እና ነጻ የሚያወጣ ብቃቱ እንዲኖራቸው የሚያደረገው እጆቻችን ከወንጀል ነጻ እና ልባችን ንጹሕ እውነትል ለማወቅ ጥረት የሚያደርግ እግዚአብሔር የሚሻ በእርሱ ፍቅር ለመነካት እና ለመለወጥ የምንፈቅድ ስንሆን ብቻ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ለሆሣዕና በዓል ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ ፍጻሜ ልክ እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት አስተምህሮ ዓርብ ስቅለት የዓመጽ ሰለባ የሆኑት ሁሉ የሚዘከሩበት ዕለት መሆኑ በማስታወስ፣ ውጥረት እና ግጭት በሚታይባቸው አገሮች እና በኮሎምቢያ እርቅና ሰላም እንዲሰፍን ተማጽነው፣ ዘንድሮ በማድሪድ የሚካሄደው 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በመጥቀስ የሁሉም አገሮች ወጣቶች ማለቂያ የሌለው የአዲስ ሕይወት ምንጭ ሆነው የእግዚአብሔር ፍቅር መስካሪያን እንዲሆኑ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.