2011-04-15 14:38:19

ብፁዕ ካርዲናል ላዮሎ፦ “ማርያም፣ ጽሞና እና ቃል”


የሃገረ ቫቲካን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት እና የሃገረ ቫቲካን መስተዳድር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ላዮሎ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የአራቱ ወንጌላውያን ምስክነር ማእከል ያደረገ ማርያም ጽሞና እና ቃል በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲናል ላዮሎ ስለ ደረሱት መጽሓፍ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱስ መጽሓፍ ዘንድ ያለው እርሱም የማርያም ስበአዊ ግኑኝነቶች እና ጽሞና በተመለከተ የሚሰጡት ምስክርነት ላይ ያተኮረ መጽሓፍ መሆኑ ገልጠው፣ በወንጌል እንደተመለከተም ማርያም አራት ጊዜ ብቻ ስትናገር እናያለን፣ ሆኖም ግን ማርያም አራት ግዜ ብቻ ብትናገርም ንግግርዋ እና የገለጠቸው ሐሳብ ጥልቅ እና ብሩህ ነው። የመጀመሪያ የማርያም ንግግር ከገብርኤል መልአክ ጋር ስትወያይ ሁለተኛ ደግሞ ኤልሳቤጥን በመድረስ ለቅድስት ኤልሳቤጥ ያሰማቸው ቃላት፣ ሶስተኛው ደግሞ ማርያም እና ዮሴፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ መቅደስ ባዩት ጊዜ ማርያም ልጄ ሆይ ስለምን እንዲህ አደርረግኸን ስትል ፈልገው ካገኙት በኋላ በእናትነት ባኅርያ መሠረት በጥያቄ መልክ የተናገረቸው ቃል እና በመጨረሻም ለአራተኛ ጊዜ በቃና ዘ ገሊና የወይን ጠጅ እኮ የላቸው…. እርሱ የሚላችሁ አድርጉ በማለት የተናገረችው ቃል መሆኑ ገልጠው፣ ቅድስት ድንግል ማርያም የቃል እናት የቃለ እግዚአብሔር እናት በመሆንዋ ብዙ ለመናገርም ሆነ ብዙ ለማለት አላስፈለጋትም።

የማርያም ጽሞና እና ጸጥታ ብርታት እና ሃይል የሚያመጣ ነው። ይኽ ደግሞ ዮሴፍ አርግዛ ባገኛት ጊዜ ተደናግጦ እያለ ሆኖም ግን ከእርሷ ጸጥታ እና ጽሞና ኃይል ከሚሰጠው ኃይል በመቀዳጀ፣ት አለ ማመኑን ፍራቱን መጠራጠሩንም አሸንፈዋል። ይህ ነው የማርያም ጽሞና አቢይ ምሥጢር። በእርሷ ጽሞና እና ጸጥታ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይገልጣል፣ በሕይወታችን እና በምንጓዝበት መንገድ የምንገናኛው ሰው የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫ መሆኑ ያረጋግጥልናል፣ በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.