2011-04-15 14:36:38

ብፁዕ አቡነ ቹሊካት፦ ድኽነት ተዋልዶ በመቆጣጠር አይቀረፍም


በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ ቹሊካት በተባበሩት መንግሥታት የኤኮኖሚ እና የማኅበራዊ ጉዳይ ምክር ቤት የሕዝብ እና የእድገት ጉዳይ የሚከታተለው ድረገት ባካሄደው ስብሰባ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ በዓለማችን ድኽነት ለማስወገድ ድኾችን ማጥፋት የሚለው ሐሳብ በሥውር በማስከተለ የሚሰበከው አመለካከት በመተቸት ድኽነት ለማስወገድ መንግሥታት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የእያንዳንዱ ሰው ልጅ ክብር በተለይ ደግሞ የቤተሰብ የተዋልዶ መብት እና ክብር ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣ ካልሆነ ግን ከዚህ ውጭ ድኽነት ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት ባዶ እና ጸረ ድኽነት ሳይሆን ጸረ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል እና በጠቅላላ ጸረ ሰብአዊነትም ነው።

ዛሬም ቢሆን ይላሉ ብፁዕ አቡነ ቹሊካት፣ ስለ ሥነ ተዋልዶ እና እድገት በሚል ርእስ ዙሪያ የሚደረገው ውይይት እንደ ማረጋገጫ የሚሰበኩት የሕዝብ ብዛት እና እድገት በተመለከተ የሚነዙት የሐሰት እማኔዎች መሠረት የሚታይ እና የሚገለጥ በመሆኑ ሕይወት መስጠት፣ ልጅ መውለድ ከማበረታታት ይልቅ እንደ ችግር እና አስፈሪ ነገር ሆኖ እንዲታይ የሚያስገድድ የሚገፋፋ ነው። ይህ ዓይነቱ አመለካከት እኔነት ማእከል ካደረገ ስግብግበት፣ ተዋልዶ መልካም፣ ነገር ግን በቁጥጥር ሥር መዋል ይኽ ደግሞ ለእኔ እና እኔ ብቻ ለሚል ስስታም ሕይወት ላይ የጸና በመሆኑ ስለዚህ ተዋልዶ ቀስ በቀስ የሚያገል ባህል ነው። ስለዚህ ይኽ አይነቱ አመለካከት ከተባበሩት መንግሥታት ዓላማዎች ውስጥ እንዱ ሊሆን አይገባም። ድኽነት መሃይማነት እና የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ለማስወገድ እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብት ለሁልም እንዲዳረስ እና አካባቢን ካደጋ ለማላቀቅ የድኾች ተዋልዶ መቆጣጠር እና ጨርሶ ማስወገድ የሚለው መፍትሔ መፍትሔ ሳይሆን ችግር ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ሥነ ተዋልዶ ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት እና ምርምር የሰው ልጅ ክብር የሚቀናቀን ጾታዊ ስሜት ትክክለኛ ባኅርዩን በማዛባት ወላጆች ልጅ ለመውለድ የማያነቃቃ የማያበረታታ የማኅበራዊ ጉዳይ ፖለቲካ በብዙ አገሮች እግብር ላይ ሲውል ይታያል፣ በአባላት ቁጥር አነስተኛ የሆነው ቤተ ሰብ የተደላደለ ኑሮ ይኖራል የሚለው ሐሰተኛ አመለካከት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እና የማስታወቂያ ተባራሪ ጽሑፎች አማካኝነት በተዘዋዋሪ መንገድ ሲሰበክ እያየን ነው።

ብዙ አገሮች ተዋልዶ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠራቸው እና ስስታም ባህል በማረማመዳችቸ ምክንያት በእድሜ የገፋው የአዛውንት ብዛት ከወጣቱ ቁጥር ብዛት እጅግ በልጦ ትልቅ መዛባት እና ግሽበት እያስከተለ ነው። ስለዚህ በዓለማችን እድገት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት የሰው ልጅ ክብር የሚጠብቅ ይኽንን ማእከል ያደረገ በሥነ ምግባር የተካነ መሆን አለበት። የሕዝብ ብዛት ለመቀነስ ዓልሞ የሚወጠነው የልማት እቅድ በማግለል የሰውን ልጅ ማእከል ያደረገ በሥነ ምግባር የተካነ እቅድ በመወጠን የተስተካከለ እውነተኛ እድገት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ የሚቻል ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.