2011-04-15 14:34:11

ብፁዕ አቡነ ቤቻራ ቡትሮስ ራይ፦ ሊባኖስ የነጻነት እና የኅብረአዊነት አገር


እዚህ በቫቲካን ረዲዮ የአረብኛ ቋንቋ የሥርጭት መርሃ ግብር አሰዳዳሪ በመሆን ለ 12 ዓመታት ያገለገሉ የሊባኖስ ፓትሪያርክ ብፅዕ አቡነ ቤቻራ ቡትሮስ ራይ ትላትና በቫቲካን ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ግኑኝነት ፍጻሜ በሰሜን አፍሪቃ እና በአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የተቀጣጠለው ሕዝባው ንቅናቄ በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሂዱት ቃለ ምልልስ፣ ሕዝባዊው አመጽ እተስፋፋ የሚሄድ እና መድረሻውም ምን እንደሚሆን አይታወቀም ስለዚህ በሊባኖስ ተጽእኖ ሊኖረው ይችል ይሆኖም፣ ሆኖም ግን ሊባኖስ የነጻነት የኅብረአዊነት እርሱም ኅብረ ባህል፣ የመድብለ ፖለቲካ ሥርዓት የሰፈነባት እና ኅብረ ሃይማኖት ተግባብቶ አንዱ ባንዱ ላይ ተጽእኖ ሳያሳድር የበላይነት ሳይሰማው በሰላም የሚኖርባት አገር ነች።

በአረብ አገሮች እየተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ አመጽ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ባንድ ወቅት ሊባኖስ የሰላማዊ የጋራ ኑሮ አርአያ ነች በማለት ለሰጡት መግለጫ የአገሪቱ እውነተኛ መለያ ለአደጋ ያጋልጣል ብለው እንደማያስቡም በማብራራት፣ ሆኖም ግን የነዚህ አገሮች ማኅበረ ክርስትያን እንደሚታየው አገሩን ጥሎ የመሰደዱ ምርጫ ከወዲሁ መፍትሔ ካላገኘ ክልሉ በአንድ ሃይማኖት ተከታዮች ሥር እየተጠቃለለ ኅብረአዊነቱን እያጣ ይሄዳል፣ በሊባኖስ ተመሳሳዩ ችግር ሊከሰትም ይችላል፣ ስለዚህ የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን የመሰደድ ምርጫ የሚያገልበት መንገድ ማፈላለጉ የሁሉም በተለይ ደግሞ የሃይማኖት መሪዎች እና የፖለቲካ የበላይ አካላት ኃላፍነት ነው።

የክልሉ ኅብረ ሃይማኖት እሰይታ እንዲታቀብ እና የክልሉ ኅብረተሰብ አለ መከፋፈል በሰላም ለመኖር እንዲችል በተለያዩ ሃይማኖትች መካከል የጋራ ውይይት ቀጣይነቱ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ በክልሉ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የጋራው ውይይት በማነቃቃት አቢይ አገልግሎት እየሰጠች ነው። እንዲሁም የእስልምና ሃይማኖት መንፈሳውያን መሪዎች እና የክርስትያን ሃይማኖት መንፈሳውያን መሪዎች በሊባኖስ መንበረ ፓትሪያርክ የጋራ ውይይት እንዲያካሄዱ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች ያቀረቡት ጥሪ በማስታወስ፣ ስለዚህ በሁሉም መስክ የሚያዋህደው ክብር ለማረጋገጥ አቢይ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ኩላዊት ቤተ ክርስትያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሎም በተለያዩ አገሮች በሚገኙት አካልዋ የሆኑት አቢያተ ክርስትያን በሚገኙበት አገር በግብረ ገባዊው ኃይልዋ መሠረት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል እንዲሁም በተለያዩ ባህሎች የጋራው ውይይት በማነቃቃት የጋራው ጥቅም እንዲረጋገጥ አቢይ ሚና በመጫወት ላይ ነች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.