2011-04-15 14:35:01

በቻይና የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት


እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፈቃድ እና ውሳኔ መሠረት የተቋቋመው በቻይና የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚንከባከበው ድርገት፣ በቻይና ስላለችው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ በተመለከተ አንገብጋቢ እና አስፈላጊ በሆኑት አበይት ጥያቄዎች ዙሪያ ለመወያየት በቫቲካን ስብሰባ እያካሄድ ነው። ድርገቱ ስብሰባውን በቻይና ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስያን የማበረታታቻ እና የድጋፍ መልእክት በማስተላለፈ እንደጀመረም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ድርገቱ ያስተላለፈው መልእክት፣ ለቤተ ክርስትያን ባለን ፍቅር ተገፋፍተን እንዲሁም በቻይና የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን የተጋረጠባቸው ፈተና እና ስቃይ ተጋፍጠው፣ በእምነት በፍቅር እና በተስፋ ለማሸነፍ ይችሉ ዘንድ፣ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ቅርብ በመሆን በማበረታታት እና ድጋፍዋን በማቅረብ የቤተ ክርስትያንዋ ዕለታዊ ኑሮ ተካፋይ መሆንዋ በማረጋገጥ፣ ጽኑ እና ኅያው እምነት በቤተ ክርስትያን ተስፋ መሠረት ከተጨባጩ ማኅበራዊ ጉዳይ ጋር ለመወያየት እና የተጋረጠባት ስቃይ እና ፈተና ለመወጣት እንደምትችል ድርገቱ ባስተላለፈው መልእክት አክሎ በማሳወቅ፣ በቻይና ካለችው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተለየው የቻይና ብሔራዊ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ቤተ ክርስትያን በምትፈጽማቸው ቅብአተ ጵጵስና በምትሰጠው የክህነት ማእርግ ምክንያት እያጋጠመ ያለው የሚያሳዝን ታሪክ በመጥቀስ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን ቅብአተ ጵጵስናው የተረጋገጠ መሆኑ ብታምንበትም ነገር ግን አለ ውሳኔ እና አለ ፈቃድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጠ በመሆኑ፣ አደገኛ ከሕግ ውጭ መሆኑ በማስታወስ፣ ስለዚህ እነዚህ የቻይና ብሔራዊ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ቅብአተ ጵጵስና የምትሰጣቸው አቡኖች ሐዋርያዊ ኃላፊነት እና አገልግሎት ከሕግ ውጭ መሆኑ በማብራራት፣ እነዚህ አቡኖች ከቤተ ክርስትያን ውጭ በሆኑት አካላት ተጽእኖ እንዳለባቸው በመገንዘብም ኩላዊት ቤተ ክርስትያን በቀጥታ እና ወዲያውኑ ለማውገዝ አልተራወጠችም፣ ሆንም ግን ይህ የተከሰተው ተጨባጭ ሁኔታ የቤተ ክርስትያን አካል እጅግ ለስቃይ አያጋለጠ ነው። ስለዚህ ቅብአተ ጵጵስና የተቀበሉት ሁሉ ከመንበረ ጴጥሮስ፣ ለምእመናን እና ለካህናት ያላቸው አቋም እርሱም ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታማኝ እና ታዛዥነታቸውን እንዲያሳውቅ ግዴታ መሆኑ ድርገቱ ጥሪ በማቅረብ፣ ይህ ደግሞ ተከስቶ ላለው ችግር መፍትሔ ነው በማለት እንደገለጠውም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

በቻይና ብፁዓን አቡናት የሚያስፈልጋቸው አበይት ሰበካዎች እንዳሉ የተረጋገጠ ነው። ይኽ ችግር ቤተ ክርስትያን በቅርብ ጠንቅቃ የምታውቀው ጉዳይ ነው። ስለዚህ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን ችግሩን ለመቅረፍ የተሰጣት ኃላፊነት እግብር ላይ ታውለውም ዘንድ ከአገሪቱ መንግሥት ቅን እና ግልጽ እንዲሁም በመከባበር ለመወያየት ጥረት እያደረገች መሆንዋ ድርገቱ ባስተላለፈው መልእክት በመጥቀስ፣ የሻንጋይ ሰበካ ፖውል ዙ ጉዋንግኪ ብፅዕና እንዲታወጅላቸው የሚደረገው ጥናት ይጀመር ዘንድ ከኵላዊት ቤተ ክርስትያን ፈቃድ በማግኘትዋም አቢይ ደስታ ነው በማለት፣ የቻይና ካቶሊክ ምእመናን ለኩላዊት ቤተ ክርስትያን ታማኝ ከመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ እንድነት እንዲኖር ያላቸው ጥልቅ ፍላጎት ዘወትር ገሃድ ከማድረግ እንዳልተቆጠቡም ድርገቱ በማስታወስ፣ ግንቦት 24 ቀን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ስለ ቻይና ቤተ ክርስትያን የሚጸለይበት ዕለት እንዲሆን ቅዱስ አባታችን የሰጡት ውሳኔ በማስታወስ ሁሉም በሁሉም አገር የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በዚህ የቅዱስ አባታችን የጸሎት ሃሳብ ተሳታፊ እንድትሆን ጥሪ በማቅረብ ድርግቱ ለቻይና ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና መእመናን ያስተላለፈው መልእክት እንዳጠቃለለ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.