2011-04-14 15:12:17

ብፁዕ ካርዲናል ታውራን፦ የሃይማኖት ነጻነት በመከላከል ማንኛው ዓይነት አድልዎ ማውገዝ


የኤወሮጳ ኅብረት ምክር ቤት በተለያዩ ባህሎች መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይት ያለው ሃይማኖታዊ አድማስ በሚል ርእስ ሥር ባካሄደው ውይይት የተሳተፉት ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው የጋራ ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን የእግዚአብሔር ለአድልዎ እና ለዓመጽ መገልገያ መሣሪያ ወይም ምክንያት አድርጎ ማቅረብ አይገባም በሚል ርእስ ሥር ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር፣ የኤውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት የሃይማኖት ነጻነት ለመከላከል ማንኛውም ዓይነት አድልዎ ለማውገዝ ቆራጥ መሆን አለበት ካሉ በኋላ በዓለም በሃይማኖት ምክንያት የሚፈጸመው አድልዎ እና ዓመጽ ኅብረቱ በመቃወም ጨርሶ እንዲወገድ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል።

ብፁዕ ካርዲናል ታውራን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እና ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብሎም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጋውዲዩም ኤት ስፐስ (ሃሴት እና ተስፋ) የተሰኘው ሓዋርያዊ ውሳኔ የሃይማኖት ነጻነት መከበር እና በምንም ተአምር በማንም መጣስ የማይገባው የሰው ልጅ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መሠረት መሆኑ የተሰጠበት ማብራሪያ እና የሚቀርበውም ጥሪ በመጥቀስ፣ ማንኛው ኃይማኖት በአስገዳጅ ሊቀርብም ሆነ ሌላው ተከታይ ለማድረግ እና ለማሳመን ተጽእኖ መሆን አይችልም፣ የኤውሮጳ ኅብረት የኅብረ ሃይምኖት እና የኅብረ ባህል አርማ ነው። የኤውሮጳ የሰብአዊነት ባህል መሠረቱም የክርስትናው እምነት ነው። ለዚህ ማረጋገጫውም የኤውሮጳ አበይት ተቋሞች የሚባሉት ትምህርት ቤቶች መናብረተ ጥበብ የሕክምና መስጫ ማእከሎች የመሳሰሉትን እንደ አብነት ለመጥቀስ ይቻላል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.