2011-04-14 15:15:30

ብፁዕ አቡነ ግሂበርቲ፦ ቅዱስ ከፈን የወንጌል መስታወት ነው


የቲዮሎጊያ እና የቅዱስ መጽሐፍ የሥነ ቅዱስ ከፈን የምርምር ጥናት ሊቅ ፕሮፈሶር ብፁዕ ኣቡነ ጁዜፐ ግሂበርቲ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ረጂና አፖስቶሎሩም መንበረ ጥበብ ቅዱስ ከፈን በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው የአንድ ቀን አውደ ጥናት ተገኝተው አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት እና ቅዱስ ከፈን በሚል ርእስ ሥር በሰጡት አስተምህሮ፣ አምልኮ እና ምርምር፣ እምነት እና ምርምር የሚነጣጠሉ እና የየራሳቸው የጥናት ሥነ አግባብ እና ዘይቤ ያላቸው ቢሆኑም እርስ በራሳቸው አይነጣጠሉም፣ አንዱ ሌላውን አያገልም ምክንያቱም ተሟይ ናቸውና። ቅዱስ ከፈን የእምነት አንቀጾች ተብለው ከሚዘረዘሩት የእምነት አንቀጾች ውስጥ እንደ አንድ አንቀጽ የሚገለጥ አይደለም፣ በጠቅላላ የእምነት አንቀጽ አይደለም። ሆኖም ግን ለማመን የሚደግፍ ቅዱስ ምልክት እና መሣሪያ ነው። ስለዚህ የሚያንቀላፋው አማኝ በእምነት የሚደክመው ምእመን የሚያነቃቃ ቅዱስ መሣሪያ ነው ካሉ በኋላ፣ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ቀጥሎም ር.ሊ.ጳ. የእዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጵውሎስ ሁለተኛ አሁንም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በወንጌል እና በቅዱስ ከፈን ዘንድ ያለው ግኑኝነት ጥልቅ እና ሰፊ አስተምህሮ መስጠታቸው ዘክረው፣ ይህ ደግሞ ቅዱስ ከፈን የወንጌል መሥታወት ነው ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ፣ እምነት እና ምርምር የሚያገናኝ እርሱም የሥነ ምርምር ዘርፍ ከፈኑ የመቼ ዘመን ዕድሜው ያታተመበት ምስል ማንነት የመሳሰሉት ላይ በማተኮር ጥናት ሲያካሂድ፣ በሌላው ረገድ የስቃይ ምስል የታተመበት በጽሞና አስተንትነኝ የሚል ጥሪ የሚያቀርብ፣ እምነት የሚያነቃቃ ነው በማለት ሲገልጡት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሕማማት ሳምንት ምሥጢር ምልክት፣ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን እጅግ የተናቀ በመሆን በሞት የሰውን ልጅ ሞት በመሞት በመቃብር በማደረ የሰው ልጅ ስቃይ ፍጹም መግለጫ የሆኑት ክስተቶች ከሰው ልጅ በላይ በጥልቀት በመኖር ቀጥሎ በትንሣኤው ለሰው ልጅ ስቃይ ትርጉም በመስጠት ዳግም ተስፋ በማልበስ፣ ተስፈኛ ለመሆን የሚያበቃ ፍጹም ምክንያት አቀረበ በማለት ቅዱስ ከፈን እንዲህ በማለት እንደገለጡት ብፁዕ አቡነ ግሂበርቲ በማስታወስማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.