2011-04-14 15:13:17

ብፁዕ አቡነ ቨሊዮ፦ ለኢራቅ ተፈናቃይ ዜጎች መብት እና ፈቃድ ጥበቃ


የስደተኞች እና ተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ፣ እ.ኤ.አ. ባለፈው መጋቢት ወር በዮርዳኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው እዛው በስደት ከሚኖሩት ከኢራቅ ተፈናቃይ ዜጎች ጋር በመገናኛት እና ያሉበት ሁኔታ ቀርበው ለመገንዘብ መቻላቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ከሐዋርያዊ ጉብኝት መልስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በርግጥ የኢራቅ ዜጎች በገዛ አገራቸው ተፈናቅለው የሚኖሩት፣ በዮርዳኖስ በሊባኖስ በሶሪያ እና በቱርክ ተሰደው የሚኖሩ ተፈናቃዮችም እንዳሉ አስታውሰው፣ የእነዚህ ተፈናቃይ የኢራቅ ዜጎች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው። በዮርዳኖስ ሶስት መኖት ሺሕ የሚገመቱ በድኽነት ምክንያት የተሰደዱ፣ ሌሎች 500 ሺሕ ተፈናቃዮች ውስጥ 33 ሺሕ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ በሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት የበላይ ድርገት እውቅና ያገኙ መሆናቸውም ገልጠው፣ ምንም’ኳ የተሟላ ድጋፍ ለማቀረብ አስቸጋሪ ቢሆንም ዮርዳኖስ ለእነዚህ የኢራቅ ተፈናቃይ ዜጎች ለማስተናገድ ፈቃደኛ በመሆንዋ ምክንያት ለዮርዳኖስ ንጉሥ አብዱላህ ሁለተኛ ማመስገናቸው ጠቅሰው፣ የኢራቅ ሕዝብ በአገሩ ካንሰራፈው ማለቂያ ካጣው ችግር እና ውጠረት በማምለጥ የሚሰደድ መሆኑና ይኽ ኅብረተሰብአዊ ክስተት አናሳው የክርስትያን ሃይማኖት ተከታይ የኢራቅ ኅብረተሰብ ክፍል ብቻ የሚመለከትም ሳይሆን የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑትንም ጭምር የሚነካ ችግር ነው ብለዋል።

በተለያዩ አገሮች ተሰደው የሚኖሩት የኢራቅ ተፈናቃይ ዜጎች ሰብአዊ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ የሚያቀርቡ የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማህበራት እንዳሉ በመግለጥ፣ አሁንም አገልግሉት እየሰጡ መሆናቸው በዮርዳኖስ ቀርበው ለመመልከት መቻላቸውንም ጠቅሰው፣ በዮርዳኖስ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በአገሪቱ ከሚገኙት የተለያዩ የመንፈሳዊ ማኅበራት ጋር በመተባበር የስደተኞች እና ተጓዦች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማቅረብ በሁሉም ዘርፍ ድጋፍ እያቀረበች ነው ብለዋል።

ስደተኛው ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን መብቱ እና ግዴታውንም አውቆ እና ተከብሮለት እራሱን ችሎ ለመኖር የሚያስችለው እድል ሊረጋገጥለት ይገባል። ስለዚህ የመሥራት መብቱ ተጠብቆለት እራሱን ችሎ እንዲኖር ይደገፍ ዘንድም ጥሪ በማቅረብ ካልሆነ ግን በበለጸጉት አገሮች ተሰደው ከሚኖሩት የኢራቅ ዜጎች በሚላክለት የገንዘብ ድጋፍ የሚተዳደር ተመጽዋጭ ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ ኤውሮጳ የመካከለኛው ምሥራቅ ስደተኞች ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባታል በማለት ይኸንን ጥሪ በማስተላለፍ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.