2011-04-14 15:14:38

ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ፦ “የሚያስደንቅ የሥነ ምርምር ውጤት”


በዓለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ እርሱም ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ዩሪ ጋጋሪ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 12 ቀን 1961 ዓ.ም. ወደ ኅዋ የመጠቀበት 50 ዓመት በተለያዩ የሥነ ምርምር ተቋሞች እና አገሮች በተለያዩ ባህላዊ መድረኮች አማካኝነት በመታሰብ ላይ ሲሆን፣ ይኸንን አቢይ የሰው ልጅ በሥነ ምርምር ግኝት ብልጽግና አማካኝነት ያረጋገጠው እርምጃ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ በመከታተል የሚያስደንቅ ወደ ላይ መውጣት በማለት የተሰማቸውን ስሜት ገሃድ ማድረጋቸውም የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 12 ቀን በሩሲያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ 06 ሰዓት ከ 50 ደቂቃ የ27 ዓመት እድሜ ጠፈርተኛ ዩሪ ጋጋሪ በሩሲያ የጠፈር ማስመጠቂያ ማእከል በመገኝት እና በመዘጋጀት ማታ ልክ 09 ሰዓት ከ 07 ደቂቃ ወደ ኅዋ በመመንጠቅ ልክ 10 ከ 55 ደቂቃ በምኅዋር የመዞር ተልእኮውን ፈጽሞ ወደ መሬት በመመለስ በዓለም ታሪክ ወደ ኅዋ ከመነጠቁት ጠፈርተኞች ውስት ቀዳሚ ጠፈርተኛ ለመሆን መብቃቱ ይታወሳል።

ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ስለዚሁ የሥነ ምርምር ግኝት በማስመልከት የተሰማቸው አድናቆት በይፍ በቫቲካን ረዲዮ በኵል እ.ኤ.አ. ነሐሴ 12 ቀን 1962 ዓ.ም. ለሕዝብ ሲገለጡ “የዓለም ሕዝብ በተለይ ደግሞ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል በዓለማችን እየተረጋገጠ ያለው የሥነ ምርምር ግኝት በቅርብ በመከታተል የሚሰማው ስሜት በመግለጥ ብቻ ሳይሆን የሥነ ምርምር ሂደት ተቀዳሚ ተካፋይ እና ተወናያን ለመሆን በተለያየ የሥነ ምርምር ዘርፍ እራሱን ለማዘጋጀት እንዳነቃቃውም ገልጠው፣ የሥነ ምርምር ግኝት የፍጥረት እና የባህርያዊ ሕግ ጌታ ለሆነው ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምስጋና እና ክብር አድርጎ ማቅረብ እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው። የሥነ ምርምር እድገት በሰው ዘር መካከል የወንድማማችነት እና የመቀቀራረብ መንፈስ የሚያነቃቃ የሰላም መሣሪያ እንዲሆኑ አደራ ማለታቸው የቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅድረ ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2000 ዓ.ም. በዚያኑ ዓመት የካቶሊክ ዓንቀጸ ሃይማኖት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ጆሴፍ ራትዚገር የቅድስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኢጣሊያ ፓሌርሞ ከተማ ተካሂዶ በነበረው የእምነት ሳምንት በተስየመው ዓውደ ጥናት ተገኘተው ባቀረቡት አስተምህሮ፣ ዩሪ ጋጋሪን በማስታወስ የሥነ ምርምር ግኘት እና የሰው ልጅ የሚጨብጠው የሥነ ምርምር ውጤት ጸረ ኅልወተ እግዚአብሔር የሚያረጋገጥ አመክንዮ ሊሆን አይችልም፣ ምክንያቱ እግዚአብሔር የለም ለማለት የሚያበቃ አመክንዮ ሊኖር እይችልም በማለት እግዚአብሔር በሥነ ምርምር ቤተ ሙከራ ውስጥ የሚፈለግ እንዳልሆነም ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.