2011-04-13 15:19:16

የር.ሊ.ጳ. ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (13.04.2011)


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ባቀረቡበት ወቅት በአውስትራልያ ጉባኤ ጳጳሳት ኣሳቢነት በመልበርን ከተማ በመካሄድ ላይ ላለው ሶስተኛው ሃገራዊ የቤተሰብ ስብሰባ ላይ ለሚገኙት ጉባኤተኞች በቪድዮ በቀጥታ ሰላምታ ምክርና ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው የትምህርቱ መክፈቻ ጸሎት ካሳረጉ በኋላ ሐዋርያ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች ከጻፈው መል እክት 8፡28 ‘እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።’ የሚለው በዋና ዋና የኤውሮጳ ቋንቋዎች ተነበበ። በጣልያንኛ ቋንቋ ስለ እያንዳንዱ ክርስትያን ቅድስና ሰፊ ኣስተምህሮ ካቀረቡ በኋላ ኣጠር ባለ መንገድ ደግሞ በእንግሊዝኛ የሚከተለውን ትምህርትና ሰላምታ ኣቅርበዋል።

“ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ባለፉት የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮዎች ያቀረብኩትን የቅዱሳን ታሪክ ለመደምደም በዛሬው ትምህርተ ክርስቶሳችን እያንዳንዱ ክርስትያን የተጠራንበት ስለ ቅድስና መናገር እወዳለሁኝ። ቅድስና የክርስትና ሕይወትን ወደ ፍጽምና የሚያደርስ ነው። ቅድስና ማለት በክርስቶስ መኖር ማለት ነው። ይህን የሚያቋቋመው ከክርስቶስ ጋር ኣንድ መሆናችን ነው። ይህ ማለትም የኢየሱስ ክርስቶስ ሓሳብንና ተግባርን የእኛው በማድረግ፤ ሕይወታችን ከሕይወቱ ጋር እንደሚስማማት ማድረግ ኣለብን። ይህ ዓይነት ህይወት በመጀመርያ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፤ እኛ መንፈስ ቅዱስን በምሥጢረ ጥምቀት እንቀበላለን፤ በዚህ መንፈስ ቅዱስም የምሥጢረ ፋሲካ ተካፋዮች እንሆናለን፤ ይህም ሱታፌ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣው ክርስቶስ ጋር ኣዲስ ህይወት ለመኖር ብቃት ይሰጠናል። የክርስትና ቅድስና የፍቅርን ጸጋ በሙላት ከመኖር ኣልፎ ሌላ ምንም ኣይደለም። በቅድስና ጉዞ የእግዚአብሔር የሕይወትና የፍቅር ዘር ቃሉን በመስማትና እተግባር ላይ በመዋል እንዲሁም በመጸለይና በቅድሳት ምሥጢራት በመሳተፍ በመሥዋዕትና ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በማገልገል ይፈጸማል። የቅዱሳን የሕይወት ታሪክ በዚሁ ለዘለዓለማዊ ሕይወት ሙላት የሚመራን ትልቅ የቅድስና ጎዳና ለመራመድ ያበረታታናል። በቅዱሳን ጸሎትና በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እያንዳንዳችን የክርስትና ጥሪኣችንን በሙላት በመኖር እግዚአብሔር በታሪክ በሚፈጥረው ትልቁ የቅድስና ሕንፃ ሕያው ድንጋይ በመሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የሚያንጸባርቀው ክብር በሙላት ኣሸብርቆ እንዲታይ ያድርግልን።’ በማለት ትምህርታቸውን ፈጽመው፤ በትምህርተ ክርስቶሱ ለተገኙት ምእመናንና ነጋድያን በተለያዩ ቋንቋዎች ኣምስግነዋል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻ በአውስትራልያ ጉባኤ ጳጳሳት ኣሳቢነት በመልበርን ከተማ በመካሄድ ላይ ላለው ሶስተኛው ሃገራዊ የቤተሰብ ስብሰባ ላይ ለሚገኙት ጉባኤተኞች በቪድዮ በቀጥታ የሚከተለውን ሰላምታ ምክርና ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል። ‘በዛቭየር ኮለጅ በመልበርን ከተማ ለሶስተኛ ሃገራዊ የቤተ ሰብ ስብሰባ ላይ ለምትገኙት ሁላችሁ የሞቀ ሰላምታየን ስልክላችሁ ደስታ ይሰማኛል። ይህ ኣስፈላጊ ፍጻሜ በእያንዳንዱ ቤተ ሰብ ያለውን የቤተ ሰብ ትስስርና ፍቅር ለመመስከር ብቻ ሳይሆን ሰፊው የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ ከሆነችው ቤተክርስትያን ጋር ኣንድ እንድታደርግዋቸው በዚህም የኣዲስ ሰብኣውነት ምስክሮች በመሆን ሁል ግዜ ለእግዚአብሔር ኣብ ክብር ለመስጠት የታደሰ የፍቅር ልማድ የህይወትና የመረጋጋት ኣራማጆች እንድትሆኑ ይረዳችህዋል፤ በጸሎቴ እንደማስባችሁ በተለይም ለሕጻናትና ለታመሙ ወገኖቻችሁ እንደምጸልይ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ለናዝሬቲቱ ቅድስት ቤተ ሰብ ሳማጥናችሁ የቅድስት መርይ ማክሎፕ ኣማላጅነትን እለምንላችዋለሁ፤ ሐዋርያዊ ቡራኬየየም እንደ የደስታና የሰላም ምልጃ እሰጣችዋለሁ።’ ሲሉ ሰላምታ ምክርና ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ትምህርታቸውን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.