2011-04-12 09:54:59

ቤተ ክርስትያን እና አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን


እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ቤተ ክርስትያን እና አዲስ የመገናኛ ብዙሃን በሚል ርእስ ሥር ለየት ባለ መልኩ በድረ ገጾች በኵል ሰዎች ወይንም ማኅበራት እና ማኅበረሰብ በየዕለቱ የሚያቀርቡት እርሱም በተለያዩ ርእሰ ጉዳይ ላይ በማተኮር በተለያየ ዘርፍ በመመልከት የሚሰጡበት የትንተና እና የማስረጃ ዜና መዋዕል ላይ ያተኮረ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በጋራ ያዘጋጁት ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ስለ ተዘጋጀው ዓውደ ጥናት በማስመልከት የባህል ጉዳይ በሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የግኑኝነት እና የሥነ ቋንቋ ጉዳይ የሚመለከት ቢሮ ተጠሪ የዓውደ ጥናቱ ደራሲ ዶክተር ሪቻርድ ሩሰ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ወቅታዊው ባህል የዜና መዋዕል ድረ ገጾች መስፋፋት የሚታይበት የተለያዩ ሰብአዊ ፖለቲካዊ ባህላዊ ፍልስፍናዊ ቲዮሎጊያዊ ባጠቃላይ በተለያዩ የምርምር እና የጥናት ዘርፎች አማካኝነት የሚነሱት ዓበይት እና አንገብጋቢ ጥያቄዎች ላይ በማተኮር የሚዘረዘሩት መልሶች እና የትንተና ዜና መዋዕል ላይ በማነጣጠር የዚህ አዲስ የድረ ገጽ ዜና መዋዕል ዓላማው ምን መሆኑ ለማወቅ፣ የዜና መዋዕል ደረ ገጾች አማንያን ኢአማንያን የዜና መዋዕል ድረ ገጽ ደራሲያን የሚሳተፉበት ዓውደ ጥናት መሆኑ ገልጠው፣ አንድ ቋንቋ ተገልጋዩን ሰው ይለውጣል ይገልጣልም ሲሉ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ያሉትን ሃሳብ በማስታወስ፣ ቤተ ክርስትያን በዚህ በሥን አኃዝ በተራቀቀው ዓለም ለምታቀርበው አስፍሆተ ወንጌል እና ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አቢይ ድጋፍ ነው ብለዋል።

ይህ አዲሱ የዜና መዋዕል ድረ ገጾች በኵሉ የውይይት ባህል ለማነቃቃት አማኙ ለአማኙ ብቻ ሳይሆን ከኢአማንያን ጋር የሚወያይበት ኅብረ ባህል የሚያጎላ፣ እያንዳንዱ ማኅበራዊ ድረ ገጽ በሚያተኩርበት ርእሰ ጉዳይ መሠረት የተዘጋ ሳይሆን በሚያተኩርበት ርእሰ ጉዳይ በኩል ከሁሉም ጋር የሚወያይ ክፍት መሆን አለበት፣ ስለዚህ ደረ ገጻዊ መለያው የሚያገል፣ ሌላውን የሚነጥል መሆን የለበትም ከሚለው አመለካከት በመንደርደር የተዘጋጀ ዓውደ ጥናት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.