2011-04-11 15:45:07

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አቢይ ጸላይ እና አስተንታኝ የክርስቶስ ሐዋርያት


ባለፈው ቅዳሜ በቫቲካን በሚገኘው የብፁዓን ካርዲናሎች የጉባኤ አዳራሽ “ነጭ ልብስ የለበሱ መንፈሳዊ ተጓዥ” በሚል ርእስ ሥር የፖላንድ ዜጋ ፊልም ቀራጭ እና ደራሲ ወጣት ያሮስላው ስዝሚድት ያዘጋጀው ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዓለማዊ ምእመን ካህን ብፁዕ አቡን ብሎም ካርዲናል በመጨረሻም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ለዓለም ሕዝብ የሰጡት ኅያው እና ብሩኅ የእምነት ምስክርነት ላይ ያነጣጠረ የትረካ ፊልም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ብፁዓን ካርዲናሎች እና ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት ለትርኢት መቅረቡ ተገለጠ። እንደሚታወቀውም ስለ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሕይወት ታሪክ በተለያየ አድማሳዊ ራእይ ላይ በማቶክረ ብዙ የትረካ ፊልም መቀረጹ እና ለትርኢት መቅረቡ ሲታወቅ፣ ሆኖም ይህ ነጭ ልብስ የለበሱ መንፈሳዊ ተጋዥ በሚል ርእስ ሥር የቀረበው የትረካ ፊልም በትክክል በጥራቱም ሆነ በአቀራረቡ የተዋጣለት መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በፊልሙ ፍጻሜ ባሰሙት ንግግር፣ በዚህ ፊልም ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የሰጡት ምስክርነት በርግጥ የእኚህ አቢይ የቤተ ክርስትያን ልጅ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማንነት ለይቶ የሚግልጥ ነው።

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አቢይ ጸላይ አስተንታኝ አቢይ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ፣ እግዚአብሔር የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ ቤተ ክርስትያንን ወደ ሶስተኛው ሺሕ እርሱን እ.ኤ.አ. ከጥር 1 ቀን 2001 በኋላ ወደ ተገባው እስከ 3000 ዓ.ም. ድረስ ወዳለው ዘመን እንዲያሸጋግሩ የመረጣቸው በቃል እና በሕይወት ካለ መታከት ሕዝበ እግዚአብሔርን የመሩ አሁን በሰማይ ቤት ሆነው እኛን በዚህ ምድራዊ ጉዞአችን እየሸኙን ናቸው ስለዚህ የተከታተኩት ፊልም ይኸንን እውነት የሚያጎላ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጵውሎስ ዳግማዊ ታሪክ የሚያወሳ የሮማ ሰበካ የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተለው ቢሮ ያዘጋጀው የሥዕል ትርኢት መከፈቱ ሲገለጥ፣ የእኚህ ዓቢያ የቤተ ክርስትያን ልጅ በሥዕል የተደገፈ መላ የሕይወት ታሪካቸው የሚዳስስ ትርኢት መሆኑ የሮማ ሰበካ የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አስተዳዳሪ አባ ማውሪዚዮ ሚረሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አብራርተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.