2011-04-07 15:39:50

የሰውን ልጅ ልብ ዳግም ለማነቃቃት


እዚህ በሮማ ሁሌ በየዓመቱ በዓቢይ ጾም የመጨረሻ የሕማማት ሳምንት ዓርብ ሥቅለት በኮሎሶዮ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተመርቶ የሚፈጸመው ፍኖተ መስቀል የአስተንትኖ እና የጸሎት መጽሓፍ የደረሱት ፈደራላዊ የቅዱስ አጎስጢኖስ የደናግል ማኅበራት ሊቀ መንበር የቅዱስ አጎስጢኖስ መናንያን ደናግል ማኅበር አባል እናቴ ማሪያ ሪታ ፒቾነ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የደረሱት የዓርብ ስቅለት የፍኖተ መስቀል መጽሐፍ ያካተተው አስተንትኖ እና ጸሎት ከቅዱስ መጽሓፍ የመነጨ በቃለ ቅዱስ መጽሐፍ ከተነካ ልብ እና በቃሉ ብርሃን አማካኝነት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከሚወያይ ልብ የመነጨ ነው። ስለዚህ የልብ ኑዛዜ እና የእግዚአብሔር ጥበቃ ለመጸለይ የሚነቃቃ ነው። ቃለ እግዚአብሔር ከማዳመጥ የሚገኝ መንፈሳዊ ጸጋ ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል።

ስለዚህ ፍኖተ መስቀል በእያንዳንዱ የመስቀል ምዕራፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመከተል የአማኝ ልብ ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ የሰውን ልጅ ልብ በማሰብ ያዘጋጁት የአስተንትኖ እና የጸሎት መጽሐፍ መሆኑ ገልጠው፣ የሰው ልብ ለገዛ እራሱ ዓለም ነው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው ሁሉ ከልብ ለሚሰጥ ውሳኔ መግለጫ ነው፣ ስለዚህ በዓለም የሚከሰተው እና በመከሰት ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ በመካከለኛው ምስራቅ እየታየ ያለው ግጭት ላይ በማሰብ በተከሰተው ላይ ብቻ ለማተኮር ሳይሆን የዚህ ሁሉ ሰብአዊ ችግር፣ መንስኤው ለመለየት በማስተንተን፣ ስለዚህ የሁሉም ክስተት መንስኤው የሰው ልጅ ልብ ነው፣ የሰውል ልጅ ይኸንን ኃላፊነቱን በመገንዘብ ይኽ ግንዛቤ ለገዛ እራሱ የእያናንዱ ሰው ልጅ ኃላፊነት ላይ እንዲተኮር የሚያግዝ ከመሆኑም ባሻገር እንደ አብነት የጃፓን ርእደ መሬት በመጥቀስ ለመደጋገፍ እና ለመተባበር የሚያነቃቃ ኃይል ይሆናል። በዓለም የሚታየው እና የሚከሰተው ሁሉ የማይመለከተው አንድም ሰው የለም፣ ይህ ደግሞ የዓለም ሕዝብ አንድ ማኅብረሰብ መሆኑ የሚያረጋገጥ እውነት ነው።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀራንዮ ጉዞ፣ በገዛ እራሱ ሰብአዊነቱ የሰውን ልጅ ሰብአዊነት እንደለወጠ፣ እርሱን እና በመስቀል መንገድ የእርሱን ዱካ በመከተል በእውነት እና በሕይወት ጎዳና በመጓዝ መስቀል ስቃይ ብቻ ሳይሆን ድልን ጭምር የሚያረጋገጥ ወደ ድል የሚያሸጋግር እውነት መሆኑ እናረጋግጣለን። ስለዚህ መስቀል የእምነት የተስፋ እና የፍቅር ማደሪያ ነው። በዚህ የመስቀል መንገድ ጸሎት አንድ ሕፃን አስተንትኖ በማንበብ እንደሚሳተፍ ገልጠው ይኽ ሱታፌ የዓለም ሕፃናት ስቃይ እና የጨቅላነት እድሜአቸው ተነጥቀው ለአመጽ የተጋለጡትን ሕፃናት ወክሎ ለበሰለው ዓለም ጥያቄ ነው ካሉ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ማእከል ያደረገ እና ቃሉም በሰው ልጅ ልብ በመግባት ልብን የሚነካ ለእውነት ገዛ እራሱን እንዲከፍት የሚያነቃቃ እግዚአብሔር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ለሰው ልጅ ድጋፉን እንደሚያቀርብ የሚያረጋገጥ አስተንትኖ እና ጸሎት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.