2011-04-07 15:40:58

የላቲን አሜሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት


እ.ኤ.አ. እስከ ሚያዝያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚቀጥል የላቲን አሜሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት በላቲን አሜሪካ ሕዝባዊ መንፈሳዊነት በአስፍሆተ ወንጌል ላይ ያለው አስተዋጽዖ/ተጽእኖ በሚል ርእስ ሥር ትላትና እዚህ በቫቲካን ይፋዊ ስብሰባውን እንደጀመረ ሲገለጥ፣ ይህ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የዚህ ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦውለት የተመራ መሥዋዕተ ቅዳሴ በማቅረብ የተጀመረው ይፋዊ ስብሰባ ተጋባእያን ነገ ዓርብ ሚያዝያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቅዱስ አባታችን ጋር በመገናኘት እና መሪ ቃል በመቀበል እንደሚፈጸም የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

የዚህ ይፋዊ ስብሰባ ዋና ዓላማ ባለፉት የላቲን አሜሪካ የአምስት ዘመን ክርስትና የላቲን አመሪካ ሕዝባዊ መንፈሳዊነት ቀርቦ ሂደቱን ለመገንዘብ እና ይህ ሕዝባዊ መንፈሳዊነት በላቲን አመሪካ የሚፈጸመው አስፍሆተ ወንጌል የሚመለከተ እና በዚህ አማካኝንነም ሕዝባዊ መንፈሳዊነት እና አምልኮ ትክክለኛ ቲዮሎጊያዊ እና ሊጡርጊያዊ ትርጉምን ጠብቆ እንዲሁም በቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት እና በትምህርተ ሃይማኖት ሥር የሚመራ መሆኑንም በመመርመር በአስፍሆተ ወንጌል የሚኖረው አስተዋጽዖ እና ተጽእኖ በመለየት ይኸንን ሁሉ መሠረት ያደረገ ተገቢ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለማቅረብ የሚያግዝ ስብሰባ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

በዚህ ከትላንትና በስትያ በተጀመረው ይፋዊ ስብሰባ የተጋበዙት ብፁዓን ጳጳሳት የዚህ የላቲን አሜርካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት አባላት እና በላቲን አሜሪካ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የዚህ ጳጳሳዊ ድርገት ተጠሪዎች የሚገኙባቸ በጠቅላላ 40 ተጋባእያን እንደሚሳተፉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.