2011-04-07 15:43:55

አዲስ ተስፋ ለመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስትያን


በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ሥፍራ እና ንብረት አስተዳዳሪ ኣባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ በሜዲትራኒያን ክልል ውሁዳን የህብረተሰብ ክፍል እና ውሁዳን ሃይማኖት በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጥናት ተገኘት ባሰሙት ንግግር፣ በአረብ አገሮች እየታየ ያለው ሕዝባዊ ለውጥ እና ንቅናቄ የክልሉ ክርስትያኖች ምን ሊያስከትልብቸው እንደሚችል በተስፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው። እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት በመግለጥ፣ የሃይማኖት ነጻነት ሃይማኖትን የመግለጡ እና የመኖሩ ነጻነት እና መብት በተለያዩ አረብ አገሮች የተጠበቀ እና የሚከበር ቢሆንም፣ የኅሊና ነጻነት ግን ዋስትና ያለው አይመስልም፣ በአረብ አገሮች በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ የነዚያ አገሮች ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች ጎን ለጎን በመሆን አብረው ያነሳሱት እና በጋራ የሚሳተፉበት መድረክ ነው። በተለይ ደግሞ በግብጽ የታየው ገጠመኝ ይመሰክረዋል። የአረብ አገሮች ዜጎች በደፈናው የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ናቸው ማለት አይደለም፣ ክርስትያን አረብም አለ። ዓረብ ቋንቋ እና ባህል እንጂ ሃይማኖትን አያሰማም፣ ስለዚህ የአረብ ቋንቋ ተናጋሪዎች የአረብ ባህል ባለ ቤት ናቸው ሆኖም ግን የአረብ ባህል የሚኖርባቸው እና የአረብኛ ቋንቋ የሚነገርባቸው አገሮች በደፈናው የምስልምን ሃይማኖት ተከታይ ዜጎች አገር ብሎ መግለጡ ስህተት ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ በማመልከት በአረብ አገሮች የሚኖረው ክርስትያን የሁዳን ሃይማኖት ተከታይ እንጂ የውሁዳን ጎሳ ማለት አንዳልሆነ አብራርተው፣ ይህ ደግሞ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር በሮማ የተካሄደው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የመጠቃለያው ሰነድ ማብራሪያ የሰጠበት እውነት መሆኑም አባ ፒዛባላ በማስታወስ ሰፊ መገልጫ እንደሰጡበት ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.