2011-04-07 15:41:52

ስደተኛው ወደ መጣበት መሸኘት ስደተኛውን በገፍ ማባረር እንዳይሆን


የኢጣሊያ መንግሥት እና የቱኒዚያ ጊዚያዊ መንግሥት መካከል ከቱኒዚያ ወደ ኢጣሊያ እየጎረፈ ያለው በብዙ ሺሕ የሚገመተው ስደተኛ ጉዳይ ማእከል በማድረግ ውይይት መካሄዱ ሲገለጥ፣ የኢጣልያ ጠቅላይ ሚኒ. ሲልቪዮ በርሉስኮኒ እና የቱኒዚያ ርእሰ ብሔር ቤጂ ካኢድ ኤሰብሲ መካከል የስደተኞች ጉዳይ ርእስ በማድረግ በተካሄደው ውይይት የተደረሰ የጋራ የስምምነት እንደሌለ ሲነገር፣ ከትላትና በስትያ ብቻ 840 ስደትኞች ላምፔዱዛ መግባታቸው ሲገለጥ፣ በሰሜን አፍሪቃ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ ምክንያት እየተሰደደ ስላለው የክልሉ ዜጋ በማስመልከት በሲቺሊያ የማዛራ ደል ቫሎ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ሞጋቨሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የክልሉ ቤተ ክርስትያን ሰውን ማእከል በማድረግ የሚሰቃየውን የሕይወት ደህንነት ለማስጠበቅ እና በተለያዩ ሰብአዊ ችግሮች ተገዶ ለሚሰደደው ተገቢ ድጋፍ ታቀርባለች፣ ሆኖም ተከስቶ ያለው የስደተኞች ጸአት ተግቢ ምላሽ መስጠት የሁሉም በተለይ ደግሞ የመንግሥታት አቢይ ኃላፊነት ነው። ስደተኛው ወደ ኢጣሊያ የሚጎርፍ በመሆኑ ችግሩ ለኢጣልያን የሚመለከት ነው ብሎ ማለፍ ሳይሆን ኃላፊነቱ የኤውሮጳ ኅበረት ጭምር ነው ብለዋል።

ስደተኛው ወደ መጣበት መሸኘት የሚለው አነጋገር በቅድሚያ አስተናጋጁ አገር በተናጥል ለብቻው የሚፈጸመው ተግባር መሆን የለበትም፣ የስደተኛው አገር የሰብአዊ መብት እና ፍቃድ ጥበቃ ምን እንደሚመስል ማጤን፣ እንዲሁም በገፍ የማባራር ተግባር መሆን የለበት የሚሉትን መመዘኛዎች ያስቀደመ ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ መሆን አለበት። የስደተኛው ማንነት እና ለስደተ የዳረገው ግላዊ ምክንያት ሳይጣራ ጠቅላይ መልስ መስጠት ትክክል አይሆንም። እያንዳንዱ የሚያቀርበው ጥያቄ በመለየት እና በማጤን ለሚያቀርበው የጥገኝነት ጥያቄ የተስተካከለ ተገቢ መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው። በሌላው ረገድ ስደተኛው በአገሩ ዕለታዊ ኑሮው ለመምራት የሚያስችለው ድጋፍ እርሱም የልማት ኤኮኖሚ ድጋፍ በሚለው እቅድ የሚሸኝ መሆን አለበት በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.