2011-04-07 15:43:00

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፦ የትምህርት እና የሕንጸት መብት


የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የቲዮሎጊያ እና የስነ ቅዱሳት ጉባኤዎች ሊቅ አባ ዳሪዩስ ኮዋልዝይች በቫቲካን ረዲዮ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔዎች ማእከል በማድረግ የጀመሩት የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ግራቪሲሙም ኤዱካዚዮኒስ ማለት መሠረታዊ ትምህርት በሚል ርእስ ሥር ብፁዓን የሲኖዶስ አበው እ.ኤ.አ. በ 1965 ዓ.ም. ያጸደቀው ውሳኔ በማስመልከት፣ የኩላዊት ቤተ ክርስትያን የማነጽ የማስተማር ተልእኮ ከንጥንት ጀምሮ ሰፊ እና ኅብረቅርጽ ያለው መሆኑ በማስታወስ፣ ስለ ትምህርት እና ሕንጸት በተመለከተ ኩላዊነት ገጽታውን የሚያመለክት መሠረታዊ መመሪያው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በማመን፣ ሁሉም ባለው የሰብአዊ ክብር ላይ የጸና አለ ምንም የጎሳ የእድሜ የጾታ ልዩነት የመማር መብት ያለው መሆኑ የሚያከብር እርሱም በሰብአዊ መብት እና ፍቃድ ላይ የተገለጠው ኩላዊ መብት መሆኑም በማስመር፣ ተቀዳሚ የሕንጸት እና የማስተማር ኃላፊነት የወላጆች መሆኑ እና የማንኛውም ሕንጸት እና ትምህርት መሠረት ቤተ ሰብ መሆኑ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በማብራራት፣ ካቶሊክ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ቤተ ክርስትያን በማቅረብ በትምህርተ ሃይማኖት እንዲታነጹ ያደርጋሉ፣ ስለዚህ የቤተ ክርስትያን ሁኔታ በካቶሊክ ቤተሰብ የሚወሰን ነው። ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የካቶሊክ ቤተሰብ መግለጫ ነች።

ሁሉም ክርስትያን ክርስትያናዊ ትምህርት የማግኘት መብት አለው። ስለዚህ ይኸንን መብት መሠረት በማድረግ ወላጆች ኅሊናቸውን በማስቀደም ካለ ምንም ተጽእኖ በነጻነት የልጆቻቸው የሕንጸት ጉዳይ ላይ የመወሰን መብት አላቸው። ስለዚህ የመንግሥት ትምህር ቤቶች የኸንን የወላጆች መብት መጠበቅ እና ማክበር ይኖርባቸዋል። ቤተ ክርስትያን ለካቶሊክ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ዘር የሕንጸት እና የማስተማር አገልግሎት ታቀርባለች፣ ሆኖም የካቶሊክ ትምህርት የማቅረቡ ተልእኮ ያላት ቢሆንም ከትምህርት ቤቶችዋ ማንንም አታገልም።

ወጣቱ ትውልድ ትምህርት የማግኘት መብታቸው እንዲከበር ጥሪ የማቅረቡም ሆነ እንዲጠበ በማድረጉ ሂደት የነቃ መሆን አለበት። በሕንጸት እና ትምህርት በማቅረቡ ኃላፊነት ተሳታፊዎች መሆናቸው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በሕንጸት ረገድ ያለውን የወጣቱ የተማሪው ኃላፊነት ጭምር ምን እንደሚመስል ያብራራል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.