2011-04-04 15:44:51

የቅድስት መንበር ርዕሰ ዓንቀጽ፦ ስለ ሁሉም ለሁሉም የፈሰሰው ደም


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና የማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በመቀጠል ትላትና ያቀረቡት ርዕሰ ዓንቀጽ ስለ ሁሉም ለሁሉም የፈሰሰው ደም በሚል ርእስ ሥር፣ በዚህ በዓቢይ ጾም ወቅት በዓለማችን በሰሜን አፍሪቃ በተለይ ደግሞ በሊቢያን እንዲሁም በአይቨርይኮስ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ RealAudioMP3 በመዘከር ለአመጽ የተጋለጠው በደል እና ግፍ እየደረሰበት ያለው የሚረገጠው የሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁሉም ቤዛ በመሆን በገዛ እራሱ ሕይወት ያሳለፈው ሰብአዊ ስቃይ ነው። እርሱ የሰው ልጅ ስቃይ ተካፋይ ብቻ ሳይሆን የራሱ በማድረግ ኖሮታል።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ለመቃወም ወይንም ሌላውን ለመጻረር የፈሰሰ ሳይሆን ስለ ሁሉም የሰው የፈሰሰ ደምነው። ሁሉም የሰው ልጅ የሚያነጻው የፍቅር ኃይል ያስፈልገዋል፣ ይህ ኃይል ደግም ቤዛችን የሆነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው። ይህ ደም ድህነት እንጂ ጥፋት እንዳልሆነ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅርቡ ለንባብ በበቃው ኢየሱስ ናዝራዊ የተሰኘው በሁለተኛው ተከታታይ መጽሓፋቸው ያብራሩት ሐሳብ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቅጹ ሥር በማብራራት፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ለአንዱ ኩነኔ ሌላው ድኅነት ሳይሆን ስለ ሁሉም ድኅነት የፈሰሰ የሚታደግ ደም መሆኑ ቅዱስ አባታችን አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አገሮች በተለይ ደግሞ በአይቨርይኮስት እና በሊቢያ እየፈሰሰ ያለው የንጹሓን ዜጎች ደም በማሰብ፣ በነዚህ አገሮች አሁን ለነገም የጥላቻ እና የብቀላ ጥማት ለማርካት የሚገፋፋ እየተስፋፋ ያለው ሁኔታ ተወግዶ ሰብአዊነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ በተሰዋው ፍቅር ሱታፌ አማካኝነት የሰላም መሠረት እንዲሆን፣ ማንኛውም ክርስትያን የሚፈሰው የንጹሓን ዜጎች ደም ሲያይ ለሁሉም ሰው ልጅ የፈሰሰው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሚያስብ አያጠራጥርም፣ እግዚአብሔር ቅርባችን ነው በሰው ልጅ ስቃይ ታካፋይም ነው፣ በሚፈሰው ደም የሚደሰተው ሰው የሰው ልጅ ጠላት ነው። እግዚአብሔር ሁሉም ያፈቅራል፣ የሁሉንም ድኅነት ይመኛል ብዙዎች ይኸንን ለመመስከር የዚህ ፍቅር ታማኝነት ለመግለጥ የደም ሰማዕትነት የሚቀበሉ አሉ፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ጉዞ እና ትንሣኤ ሰላምን ለመገንባት የሚደረገው አስቸጋሪው ጉዞ የሚደግፍ እና የሚያጸና ነው በማለት ርዕሰ ዓንቀጹን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.