2011-04-04 15:43:51

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የጋራ ውይይት እና ጸሎት አለ ምንም ግዴታዊ ተዋህዶ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 1986 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አነሳሽነት በዓለማችን ሰላም እንዲረጋገጥ የተጀመረው የአሲዚው ዓለም አቀፍ የጋራ ውይይት እና ጸሎት ቀን 25ኛ ዓመቱን ማስቆጠሩ ሲገለጥ፣ ይኸንን ታሪካዊ ቀን ለየት ባለ መልኩ ለማስታወስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ጥር አንድ ቀን የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች RealAudioMP3 ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለጋራ ውይይት እና ጸሎት ጥሪ ማቅረባቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ስለ ጥሪው መርሃ ግብር በተመለከተ ባለፈው ቅዳሜ በቅድስት መንበር የዜና የምኅተም ክፍል መግለጫ ተሰጥቶበታል።
ይህ የእውነት እና የሰላም መንፈሳዊ ነጋድያን በሚል ርእሰ ጉዳይ ተመርቶ የሚከናወነው የሁሉም ሃይማኖቶች መንፈሳውያን መሪዎች የጋራ ውይይት እና ጸሎት ቀን በዓለማችን ሰላም እና ፍትኅ እንዲረጋገጥ ለማነቃቃት ስለ ሰላም እና ፍትህ የሚስተነተንበት ውይይት የሚደረግበት እና የሚጸለይበት ቀን እንደ ተለመደው በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከተማ አሲዚ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህ መርሃ ግብር በር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልዩ ፍላጎት እና አነሳሽነት የተጀመረ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማስታወስ፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአሲዚ ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ለጸሎት እና ለጋራ ውይይት ጥሪ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ከሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
የዛሬ 25 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሁሉም የተለያዩ አቢያተ ክርስያን መንፈሳውያን መሪዎች የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች በአሲዚ ከተማ በጋራ ለጸሎት እና ጾም ብሎም ለመንፈሳዊ ንግደት ያቀረብኩት ጥሪ ተቀብላችሁ በጋራ የምናሳየው ተሳትፎ በዓለም እና ለዓለም አቢይ ምስክርነት ነው። በዚህ መርሃ ግብር ለመሳተፍ ስለ መጣችሁ አመስጋነለሁኝ በማለት በአሲዚ ለተገኙት ለሁሉም መንፈሳውያን መሪዎች ባሰሙት ንግግር ሰላምታን በማቅረብ እንዳሰጀሩ የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል በማስታወስ፣ ዘንድሮ እንዲከናወን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያቀረቡት ጥሪ የሰው ልጅ እውነትን እና መልካምን በመፈለግ የሚጓዝ የሚኖር አማኙም የኅብረተሰብ ክፍል በዚሁ ረገድ ወደ እግዚአብሔር ያቀና መሆኑም በማብራራት፣ ወደ እውነት የሚደረገው ጉዞ የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች ምሁራን ሊቃውንት የሚያገናኝ የጋራ አካፋይ የሆነ ዝንባሌ እና ጥሪ ነው፣ ይህ ደግሞ በዓለም ስለ ሰላም እና ስለ ፍትህ በሚገባ ተግቶ ለማገልገል የሚል የጋራ ኃላፊነት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜና የማኅተም ክፍል መግለጫ በማመልከት እያንዳንዱ መለያው አቅቦ አለ ምንም ግዴታዊ ውህደት የሚወያይበት እና በጋራ የሚጸልይበት ቀን መሆኑ ቅዱስ አባታችን ማብራራታቸው ለማወቅ ተችለዋል።
ቅዱስ አባታችን ለሁሉም ሃይማኖት እና ለተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መሪዎች ባስተላለፉት ጥሪ በአሲዚ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሚከናወነው የጋራ ውይይት እና ጸሎት ዋዜማ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ከሮማ ሰበካ ምእመናን ጋር በሚፈጽሙት ጸሎት እና አስተንትኖ ሁሉም በአካል እና በመንፈስ ይሳተፍ ዘንድ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል በመግለጥ፣ የአሲዚ ኖቸራ፣ ኡምብራ ጉኣልዶ ታዲኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ሶረንቲኖ የአሲዚ ቅዱሳት ሥፍራ ጠባቂ አባ ኤጂዲዮ ካኒን ጋር በመሆን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ስለ ሚካሄደው የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራ የውይይት እና የጸሎት መርሃ ግብር በማስደገፍ ጋዜጣዊ መግልጫ መስጠታቸውም የቅድስት መንበር የዜና የማኅተም ክፍል ከሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.