2011-03-21 14:16:44

የቅዱሳን ምስክርነት የክርስቶስ ኅላዌ የሚገልጥ ብልጭታ ነው


እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለበዓለ ፋሲካ ማዘጋጃ በቅድስት መንበር ቅዱስ አባታችን እና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የቅድስት መንበር ዓበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎች እና ጳጳሳት የሚሳተፉበት የቀርመሎሳውያን ገዳማውያን ማኅበር አባል ፈረንሳዊ ካህን አባ ፍራንሱዋ ማሬይ ለዘል የቅዱሳት መስክርነት የክርቶስ ኅላዌ አመልካች ነው በሚል ርእስ RealAudioMP3 ተመርቶ ሲካሄድ የሰነበተው ሱባኤ ባለፈው ቅዳሜ እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅድስት ቤተ ክርስትያን የኩላዊት ቤተ ክርስትያን ጠባቂ እና እንዲሁም የቅድስት አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ስም የሆነው ቅዱስ ዮሴፍ ዓመታዊ በዓል ባከበረችበት ዕለት መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን በሱባኤው ፍጻሜ ባሰሙት ስብከት፣ ይህ ለበዓለ ፋሲካ ማዘጋጃ የተካሄደው ሱባኤ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ጠባቂዋ እና የሳቸው ቅድስ ስም የሆነው ቅዱስ ዮሴፍ በምታከብርበት ዕለት መጠናቀቁ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስትያን ያለው አሳቢነት የሚያረጋግጥ ምልክት መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስ ዮሴፍ ትሁት ሠራተኛ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠባቂ አባት ለመሆን የበቃ፣ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ቅዱስ ዮሴፍን ቅን ሰው በማለት ይገልጠዋል፣ ቅን ሰው በቅዱስ መጽሓፍ አነጋገር እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚኖር፣ በቃለ እግዚአብሔር የሚመራ፣ የእግዚአብሔር ሕግን እንደ ጫና ሳይሆን የደስታ ምንጭ መሆኑ በማመን ሕጉን የሚጠብቅ በጠቅላላ የእግዚአብሔር ሕግ እንደ ወንጌል የሚኖር ማለት መሆኑ ካብራሩ በኋላ፣ ቅዱስ ዮሴፍ በእግዚአብሔር ፈቃድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቂ አባት እንዲሆን መጠራቱ እና ይኸንን ጥሪው በመኖር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ጠባቂ መሆኑ ቅዱስነታቸው የቅዱስ ዮሴፍ ተልእኮ ምን እንደሚመስል ገልጠው፣ የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች በተለይ ደግሞ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቤተ ክርስትያንን በመምራት ኃላፊነት ላይ የተጠሩት ትሁታን አገልጋዮች ሆነው እንዲገኙ እና በእርሱ ጥበቃ ሥር ጥሪያቸውን በቆራጥነት በመኖር ሕዝበ እግዚአብሔርን እንዲመሩ በቅዱስ ዮሴፍ አማላጅነት ጸልየዋል።

ቅዱስ አባታችን ሱባኤውን ለመሩት ለሰባኬ ኣባ ለዘልን የምስጋና መልእክት በማስተላለፍ በተለይ ደግሞ እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ቤተ ክርስያን በይፋ ብፅዕና የምታውጅላቸው ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የመንፈሳዊነት ጉዞ ጀምረው በየእለቱ የተለያዩ አበይት የቤተ ክርስያን ቅዱሳት ሊቃውንት መሠረት በማድረግ በመጨረሻም በቅዱስ ዮሴፍ መንፈሳዊነት ያጠናቀቁት የስብከት መርሃ ግብር ቤተ ክርስትያንን በበለጠ ለማወቅ እና እንድትፈቀር በማድረግ ተልእኮ የሚደግፍ የቅዱሳን ምስክርነት በገዛ ራሱ ላይ የሚቀር እና ወደ ገዛ እራስ ሌሎችን የሚስብ ሳይሆን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅላዌ የሚመለክት ብልጭታ መሆኑ በጥልቀት በማስረዳት የሰጡት ስብከት የሚያስደስት መሆኑ ባስተላለፉት መልእክት ገልጠዋል፣

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳና በሁሉም ብፁዓን ካርዲላኖች እና ብፁዓን ጳጳሳት ስም ለቅዱስ አባታችን የመልካም ቅዱስ ስም ቀን ተምኝተዋል። ከተለያዩ የአቢያተ ክርስትያን የበላይ መንፍሳዊያን መሪዎች እና የኢጣሊያ ሬፓብሊክ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ የሚገኙባቸው ከተለያዩ የመንግሥት የበላይ አካላት እና መንፈሳውያን ማኅበር የቅዱስ ስም ደስታ መግለጫ መልእክት መተላለፉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.