2011-03-21 14:23:15

ሕፃናት እና የመገናኛ ብዙሃን መርሃ ግብር


በኢጣሊያ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. ሕፃናት እና የመገናኛ ብዙኃን በሚል ርእስ ሥር የቀረበው የጥናት ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ የመገናኛ ብዙሃን መርሃ ግብሮች ሕፃናትን እግምት ውስጥ የማያስገቡ የጎልማሳው እና የወጣቱ የኅብረተሰብ RealAudioMP3 ክፍል ፍላጎት ላይ ብቻ ያተኮሩ እና የዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ራስ ወዳድነት ላይ ያነጣጠሩ በመሆናቸው ምክንያት በኢጣሊያ የመንግሥት እና የግል የቴሌቪዥን ሥርጭቶች የሕፃናት የሰዓት ገደብ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው እርሱም ሕፃናት ወደ መኝታ የሚሄዱበት የሰዓት ገደብ መሠረት በማድረግ የሕፃናት ሰብአዊ እድገት የሚያሰናክል ማንኛውም ዓይነት የቴሌቪዥን መርሃ ግብር እንዳይተላለፍ የሚለው የሕጻናት የሰዓ ገደብ የማክበር ውሳኔ በተደጋጋሚ መጣሱ ሰነዱ ያመለክታል።

የቴሌቪዥን መርሃ ግብር እና ሕፃናት በሚል ርእስ ሥር የቀረበው የጥናት ዘገባ የቴሌቪዥን የሥርጭት መርሃ ግብሮች የሕፃናት የሰዓት ገደብ በሚል መጠሪያ የሚታወቀ እርሱም ሕፃናት ወደ መኝታ የሚሄዱበት የሰዓት ገደብ መሠረት በማድረግ የሕፃናት ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲከበር የሚያዘው ደንብ የሚደገፍ እና ይኽንን ውሳኔ የሚያብራራ ባህል እንዲሥፋፋ ጥረት አለ ማድረጋቸውም ሕጻናት እና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ ሊቀ መንበር ፍራንኮ ሙገርሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ የመገናኛ ብዙኃን ላቅመ አዳም ባልደረሱት የኅብረተሰብ አባላት ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ዙናሚ በማለት ሰይመው፣ አንዴ በዓመት ዘገባ በማቅረብ የደንብ መጣስ ማመልከት ሳይሆን የሕጻናት እድገት ላለ ማሰናከል የሚደገፍ ባህል በሚገባ ማስፋፋት ወሳኝ እና ተገቢ ነው ካሉ በኋላ ወላጆች ልጆቻቸውን ለቴሌቪዥን ሞግዚትነት እንዳይተዉ ልጆቻቸው ሊከታተሉት እና ሊከታተሉት የማይገባቸውን የቴሌቪዥን መርሃ ግብር ሥርጭት በመለየት ሂደት ተቀዳሚ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማብራራት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.