2011-03-21 14:19:15

ሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ


ቅዱሳት ምሥጢራት እና ከቅዱሳት ምሥጢራት ጋር በተያያዘ ጉዳይ ለኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሕገ ቀኖና አስከባሪ መንበር አቢየት የሚባልባቸው አበትይ ጉዳዮች በመለየት የተኃድሶ ሕንጸት የሚሰጥበት ዓወደ ጥናት ዛሬ በቅድስት መንበር በሐዋርያዊ RealAudioMP3 ቤተ ኑዛዜ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

የዚህ የተኃድሶ እና ቅዱሳት ምሥጢራት መሥራት እና ማስተዳዳር በጥልቀት የሚያስረዳ ዓወደ ጥንና ተሳታፊዎች በቅርቡ የክህነት ማዕርግ የተቀበሉት አዳዲስ ካህናት የሚመለከት ሲሆን፣ አዲስ ካህን የዚህ አቢይ አገልግሎት ተልእኮው እንደጀመረ በሚከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እና ቅዱሳት ምሥጢራት በማስተዳዳሩ ተግባር ሊከተለው የሚገባው ደንብ እና ሥርዓት ጠንቅቆ እንዲያውቅ እና በተለይ ደግሞ ምሥጢረ ንስሐ በተመለተከተ የሚሰጠው አገልግሎት በጥልቀት እና በጥንቃቄ ለማስተዳደር እንዲችል የሚያግዘው የዚህ ምሥጢር ዓላማ በተመለከተ የተሟላ እውቀት እንዲኖረው የሚደገፍ የሕንጸት መርሓ ግብር መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ዓውደ ጥናቱን በንግግር ያስጀመሩት የሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ አቢይ አበ ነፍስ ብፁዕ ካርዲናል ፎርትናቶ ባልደሊ መሆናቸው ሲገለጥ፣ የእየሱሳውያን ማህበር አባል የሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ የቲዮሎጊያ ጉዳይ ተጠሪ አባ ዣን ዳንኮክ፣ የሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ ምክትል አቢይ አበ ነፍስ ብፁዕ አቡነ ጃንፍራንኮ ጂሮቲ፣ የሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ የሕገ ቀኖና ጉዳይ ተጠሪ የሕግ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኹዋን ኢግናዚዮ አሪየታ ኦቾአ ደ ቹንቸትሩ፣ በሳሊዚያን ጳጳስዊ መንበረ ጥበብ የሊጡርጊያ እና የሥነ ቅዱሳት ምሥጢራት እና የሥነ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መምህር የዚሁ መንበረ ጥበብ የቲዮሎጊያ የጥናት ዘርፍ ሊቀ መንበር የሳሊዚያን ማኅበር አባል አባ ማንሊዮ ሶዲ፣ እና ብፁዕ አቡነ ዣን ማሪየ ጀርቫይስ የሐርያዊ ቤተ ኑዛዜ ምክር ቤት አባል መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.