2011-03-18 13:46:28

ጃፓን፣ የአቶም ጨረር መጠን መጨመር ያሳደረው ሥጋት


በሰሜናዊ ምሥራቅ የጃፓን ክልል በተከሰተው ርእደ መሬት እና ድህረ ርእደ መሬት በሚታየው የመሬት መናጋት አደጋ፣ አሁንም እየቀጠለ ሲሆን፣ በተከስተው ርእደ መሬት ወደ 20 ሺሕ የሚጠጋው የአገሪቱ ሕዝብ ሰለባ መሆኑ ይነገራል።
በተከሰተው ርእደ መሬት ሳቢያ በፉኩሺማ የሚገኘው የአቶሚክ ኃይል ማመንጫ ማእከል ላይ የደረሰው የፍንዳታ አደጋ ሳቢያ በክልሉ የተረጨው የአቶም ጨረር መጠን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ሲገለጥ፣ በርእደ መሬት ሳቢያ የተጠቁት RealAudioMP3 የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ማእከል የሚያስከትለው አደጋ ለመግታት የሚደረገው ርብርቦሽ እየቀጠለ ሲሆን፣ የፉኩሽማ የአቶም ኃይል ማመንጫ ለማቀዝቀዝ የሚደረገው ጥረት እየቀጠለ ቢሆንም ቅሉ በክልሉ ያለው የአቶሚክ ጨረር መጠን እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ የአቶሚክ ኃይል ማመንጫ ማእከል ለማቀዝቀዝ የሚደረገው ሙከራው እያሰናከለ መሆኑ ነው የሚነገረው።
የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ማእከል የሚቆጣጠረው ተፓኮ በመባል የሚጠራው ድርጅት በአቶሚክ ኃይል ማመንጫ ማእከል የሚገኙት ጋኖች ለማቀዝቀዝ ተብሎ የተደረገው ቀዝቃዛው ውኃ የመርጨቱ ተግባር የአቶሚክ ጭረር መጠን ከፍ እንዲል እያደረገ ነው ሲል መፍትሔው ተጨማሪ ችግር እንደሚያስከትል ሲያመለክት በተከሰተው ርእደ መሬት ሳቢያ አምስት ሺህ ለሞት አደጋ መጋለጣቸው እና ሌሎች ከ 10 ሺህ በላይ የሚገመቱት ገና አለ መገኘታቸው ሲገለጥ፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት መግለጫ እንደሚያመለክተውም ከሆነ በጃፓን ያለው ሁኔታ የቶኪዮ መንግሥት የደረሰው አደጋ በማስመልከት እየሰጠው ካለው መግለጫ በላይ መሆኑ ታውቀዋል፣ ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ አገራቸው ለጃፓን ሕዝብ በሁሉም መስክ ለመተባበር እና ለመደገፍ ዝግጁ መሆንዋ ከጃፓን መራሔ መንግሥት ናኦቶ ካን ጋር በስልክ ባካሄዱት ግኑኝነት እንዳረጋገጡላቸው ሲነገር ተመሳሳይ መልእክት ከሩሲያው መንግሥት ጭምር መተላለፉ ለማወቅ ሲቻል፣ ሁሉም አገሮች በጃፓን የሚገኙትን ዜጎቻቸው ጃፓንን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን፣ ብዙዎችም ጃፓንን ለቀው እየወጡ መሆናቸው ይነገራል።
የፉኩሺማ የአምቶሚክ ማመንጫ ማእከል ላይ የደረሰው ጉዳት ለማስወገድ በተወጠነው እቅድ በመሰማራት ላይ የሚገኙት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ባለ ሙያዎች በክልሉ ያለው የአቶም ጨረር መጠን እጅግ አደገኛ በመሆኑ ምክንያት የአቶሚክ ኃይል ማመንጫው ማእከል ለማቀዝቀዝ የሚደረገው ሙከራ አጥጋቢ ውጤት እንደማይኖረው ይናገራሉ።







All the contents on this site are copyrighted ©.