2011-03-18 13:44:50

የቅዱሳን ምስክርነት የክርስቶስ ኅላዌ የሚገልጥ ብልጭታ ነው


እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ለበዓለ ፋሲካ ማዘጋጃ በቅድስት መንበር ቅዱስ አባታችን እና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የቅድስት መንበር ዓበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎች እና ጳጳሳት የሚሳተፉበት የቀርመሎሳውያን ገዳማውያን ማኅበር አባል ፈረንሳዊ ካህን አባ ፍራንሱዋ ማሬይ ለዘል የቅዱሳት መስክርነት የክርቶስ ኅላዌ አመልካች ነው በሚል ርእስ የሚመራው ሱባኤ እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ RealAudioMP3 ትላትና በተካሄደው አምስተኛው የሱባኤ ቀን አባ ፍራንስዋ ማሪየ ላዘል በቅዱስ ቶማሶ ዘ አኵይኖ፣ በቅድስት ተረዛ ዘ ሲየና እና በቅዱስት ጆቫና ዘ አርኮ ማእከል ያደረገ የሱባኤ አስተምህሮ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ሰባኬ ኣባ ለዘል ቅዱስ ቶማስ ዘ አኵይኖ የቤተ ክርስትያን ሊቅ የእምነት ሥነ ምርምር የቲዮሎጊያ ብርሃን መሆኑ ያሠመረበት ጥልቅ መንፈሳዊ እና ቲዮሎጊያዊ ብሎም ፍልስፍናዊ ጥናቱን በመተንተን ቀጥለውም የቤተ ክርስትያን ሊቅ ቅድስት ተረዛ ዘ ሴይና፣ ቤተ ክርስትያን ታዛዥ እና ውብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽሪት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አካል መሆንዋ ላይ ያተኮረ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም ማእከል ያደረገ የኖረቸው በቃል እና በሕይወት የሰጠቸው የእምነት ምስክርነት ላይ በማተኮር በመጨረሻም፣ ቅድስት ጆቫና ዘ አርኮ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ተጨባጭ እና መንፈሳዊነት ባህርይ ያላት እግዚአብሔር በእርስዋ አማካኝነት እውነቱን እና የተትረፈረፈ ጸጋውን እንደሚለግስ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የአሕዛብ ብርሃን በተሰኘው የትምህርተ ሃይማኖት ውሳኔ ላይ ያለው ቤተ ክርስትያን የጌታችን ኢየሱስ አካል ነች የሚለው ውሳኔ አስቀድማ የኖረች እና በማስተንተንም የመሰከረቸው እውነት እንደሆነ በማብራራት ሰፊ እና ጥልቅ አስተምህሮ በማቅረብ አምስተኛው የሱባኤው ቀን ማጠናቀቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.