2011-03-18 13:47:39

ኤውሮጳ፣ በክርስትያን ምእመናን ላይ የሚፈጸመው በደል እና አድልዎ


ከትላትና በስትያ የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀው በኤውሮጳ በክርስትያኖች ላይ የሚፈጸመው በደል እና አድልዎ ማእከል ያደረገ ዓወደ ጥናት በብራሰልስ የህብረቱ የሕዝብ ተመራጮች ምክር ቤት የጉባኤ አድራሽ RealAudioMP3 መካሄዱ ሲገለጥ፣ በዚህ በተካሄው ዓውደ ጥናት የተሳተፉት በኒው ዮርክ መንበረ ጥበብ አስተማሪ የሕግ ሊቅ ፕሮፈሰር ጆሰፍ ዋይለር ባቀረቡት አስተምህሮ መከፈቱም የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንሳ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

በክርስትያኖች ላይ የሚፈጸው መደል እና አድልዎ የሚከታተለው በኦውስትሪያ የሚገኘው ማእከል አስተዳዳሪ ጉርዱን ኩግለር በነዚህ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በኤውሮጳ በክርስትያኖች ላይ የሚፈጸመው በደል እና አድልዎ ከፍ እያለ መምጣቱ ሲገለጡ፣ በክሮአዚያ አንዲት የመንበረ ጥበብ መምህር በሶዶማዊ ጾታዊ ስሜት ጉዳይ በተመለከተ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውሳኔ እና አመለካከት ምን መሆኑ በመግለጥ እና ይኸንን ጉዳይ በተመለከተ ከቤተ ክርስትያናቸው የተሰጠው ውሳኔ እንደሚከተሉ በመናገራቸው ምክንያት ብቻ ለፍርድ መቅረባቸው ሲያስታውሱ፣ ፕሮፈሰር ሉርደስ ሩአና ኤስፒና በስፐይን ያለው የክርስትያኖች ሁኔታ ሲያብራሩ፣ በስፐይን ማንኛውም አይነት ሃይማኖት ከማኅበራዊ ጉዳይ የመነጠሉ ተግባር እጅግ እየተስፋፋ ነው ሲሉ፣ ፕሮፈሰር ሪቻርድ ኮሚኪ በታላቋ ብሪጣኒያ ያለው ሁኔታ ሲገልጡ፣ አንዲት የአይሮፕላን ተጓዞች አስተናጋጅ በአንግታቸው ላይ ያጠለቀቁት የመስቀል ምልክት የተንጠለጠለበት ኃብል እንዲያወልቁ መገደዳቸው እንደ አብነት በመጥቀስ የሃይማኖት ነጻነት እየተገታ ብቻ ሳይሆን እምነት መግለጥ የሚያጥላላ ባህል እየተስፋፋ መሆኑ ባቀረቡት አስተምህሮ አብራርተዋል።

ፕሮፈሰር ማሲሞ ኢንትሮቪኘ በኤውሮጳ ሃይማኖትን የሚጠላ ጸረ ሃይማኖት እና ምእመናን የሆነ ፀንፈኛ የፖለቲካ ርእዮት እየተስፋፋ መሆኑ በስፋት ማስረዳታቸው ሲገለጥ፣ የአይሁድ ሃይማኖት ምእመን ፕሮፈሰር ጆሰፍ ዋይልለ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሚያስደነግጠው እየተስፋፋ ያለው ጸረ ክርስትያን አምለካከት ሳይሆን የሚከሰተው አድልዎ እና በደል በዝምታ የሚያየው ሕዝብ ብዛት ከፍ እያለ መጣቱ እና ይኸንን ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያናጋው ችግር በመቃወም በይፋ የሚቀርብ ተቃውሞ አለ መኖሩ ነው። ስለዚህ በኤውሮጳ እየተስፋፋ ያለው ጸረ ክርስትያን ሃይማኖት ተግባር እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ካብራሩ በኋላ በዓለማችን በስፋት ለስደት እና ለመከራ የተጋለጠው ሃይማኖት የክርስትናው ሃይማኖት ነው ብለዋል።

የተካሄደው ዓውደ ጥናት ካዘጋጁት ውስጥ አንዱ የኤውሮጳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በኢጣሊያ በምምራት ላይ ያለው የፖለቲካ ሰልፍ አባል ማሪዮ ማውሮ ይላሉ በዝምታ እየታየ ያለው በክርስትያኖች ላይ የሚፈጸመው በደል እና አድልዎ በጣም አደገኛ መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ስለ ጉዳይ በብሔራውም ሆነ በዓለም አቅፍ ደረጃ ውይይት ተደርጎበት መፍትሄ ማግኘት የሚገባው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.