2011-03-18 13:48:39

አልጀሪያ፣ የፍትሕ እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ጥማት


በአልጀሪያ የላጉኣት እና ጋርዳያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ክላውደ ራውልት በሰበካቸው በየወሩ በሚታተመው አምጽሔት በኩል የፍትሕ እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ጥማት በሚል ርእስ ሥር ባቀረቡት ጽሑፍ በአረብ አገሮች RealAudioMP3 እየተዛመተ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ መሠረት ሲገልጡ፣ ይላሉ በጠቅላላ የአረብ አገር ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች ካላቸው የፍትሕ እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥብቃ ጥማት የመነጨ ነው፣ እየተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለመግትት የሚደረገው ጥረት የሚያስከተለው አመጽ የሚያሳዝን ነው። ሆኖም ግን የሕዝብ ጥያቄ እና ድምጽ ለማፈን የሚደረገው ጥረት በሰው ሕይወት ላይ አቢይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ብቻ ሳይሆን፣ እየታየም ነው። ስለዚህ ማኅበራዊ ፍትህ እንዲረጋገጥ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ጥያቄ እንደ ሕገ ወጥ ተግባር በማየት ለማፈን የሚደረገው ጥረት፣ ዘላቂነት የሌለው ምናልባትም እንቅስቃሴው የሚጠይቀው ለውጥ ሊያዘግይ ይችል ይሆናል ሆንም ግን የሕዝብ የፍትህ እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ጥማት የሚያረካ ባለ መሆኑ፣ ተመልሶ በተለያየ መልክ የሚከሰት ነው ካሉ በኋላ አክለውም የአንድ ሃይማኖት ምእመናን ያነሳሳው ሕዝባዊ ጥያቄ ሳይሆን አለ ሃይማኖት ልዩነት የአረብ አገሮች ዜጎች የዴሞክራሲ የፍትህ የሰላም የሰብአዊ ሕይወት መከበር የሚሉትን ጥያቄዎች በማንገብ የተቀጣጠለ ነው።

ሆኖም በመቀጣጠል ላይ ያለው ሕዝባዊ አመጽ በሚገባ ማስተዳዳሩ እና የሚጠይቀው ዓላማ ግቡን እንዲመታ የሚያግዝ ብቃት ያለው አካል ያስፈልገዋል። ስለዚህ የታሪክ ሂደት የሚያቀርበው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ አለ መስጠት ወይንም ማፈን ማኅበራዊ ውጥረቱን ያባብሰዋል እንጂ መልስ አይሆንም። ይኸንን ጉዳይ ማኅበረ ክርስትያን በትህትና በመመልከት ታሪክ ሠሪው የታሪክ ባለ ቤት እግዚአብሔር መሆኑ ካለው እምነት የመነጨ በክርስቶስ መምስለ ጥሪ የሚመራ ነው። ይክ ደግሞ የክርስትያን ኃይል መሆኑ አብራርተው፣ ማኅበረ ክርስትያን ለፍትህ እና ለእውነት በማገልገል፣ ጸረ ፍትህ እና ጸረ እውነት የሆነውን ተግባር በሰላማዊ መንገድ እና በቃል እና በሕይወት በተሸኘ ምስክርነት በመቃወም የሰላም መሣሪያ በመሆን ተግባር እንዲተጋ በማሳሰብ እና ሰላም የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑ በማመን፣ በዚህ የአቢይ ጾም ወቅት በዚሁ ጉዳይ ላይ እንዲስተነተን ለአልጀሪያ ማኅበረ ክርስያን አደራ በማለት ያቀረቡት ጽሑፍ እንዳጠቃለሉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.