2011-03-14 14:39:56

የቅድስት መንበር ርዕሰ ዓንቀጽ፦ የቅ.አ. ር.ሊ.ጳ “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛ ተከታታይ መጽሓፍ ለእኛ የፍስሃ ምክንያት የሆነ አቢይ ጸጋ ነው።


እ.ኤ.አ. መጋቢት 10 ቀን በሁሉም ቤተ መጻሕፍት ለአንባቢያ የቀረበው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛ ተከታታይ መጽሐፍ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦውሌት፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ፕሮፈሶር ክላውዲዮ ማግሪስ እና የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል RealAudioMP3 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ለንብባብ የበቃው መጽሓፍ አባ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀረቡት የቅድስት መንበር ርዕሰ ዓነቀጽ መጽሐፉ ለእኛ የፍስሃ ምክያት የሆነ አቢይ ጸጋ ነው በሚል ርእስ ሥር ሲያቀርቡ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ኢየሱስ ናዝራዊ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ ሁሉም ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ለሚፈልግ የሚጠቅም ነው። “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛው መጽሐፍ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም ንጉሥ መሆኑ የሚገልጠው ወደ ኢየሩሳሌም መግባት ከሚለው ታሪክ በመጀመር በጠቅላላ እስከ ትንሣኤ እና ዕርገት ያለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ቅዱስ አባታችን የቲዮሎጊያ ሊቅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት እና በጥልቅ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥልቅ ጉዞ የሚመሰክር እና የዚህ ጥልቅ መንፈሳው ሰብአዊ እና የቲዮሎጊይ ሊቅነት ጎዞ ውጤት መሆኑ አባ ሎምባርዲ በማብራራት፣ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ኦውለት መጽሐፉ ለንባብ በቀረበበት ዕለት ባሰሙት ንግግር፣ ይሕ መጽሐፍ ያለው ታሪካዊ አስፈላጊነት አቢይ ነው በማለት እርሱም አዲስ የቲሎጊያ የቅዱስ መጽሓፍ ሥነ ትንተና በር የከፈተ መሆኑና ቅዱስ አባታችን የቲዮሎጊያ እና የፍልስፍና ሊቅ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን እረኛ የክርስትና እምነትና ባህል መሠረት የሆነው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመረዳት የሚያግዝ የተሟላ ጥልቅ እና መሠረታዊ መርኅ መሥመር ሰጥተውናል።

ቅዱስነታቸው አዲስ የታሪክ ሥነ አቃቂር ባህል እና የእምነት ሥነ ትንተና በቃል እና በሕይወት ከሚኖሩት ሥነ እውቀት እና እምነት መሠረት ወንጌል እንዴት ለመረዳት እና በጥልቅ ለማወቅ እንድንችል የሚያግዝ አንድ አዲስ በቂ እና ሙሉ ጽማሬ ሐሳብ እንዳቀረቡ አባ ሎምባርዲ ገልጠው በማያያዝ እንዲሁም መጽሐፉ ለንባብ ለማቀረብ በተሰጠው ጋዘጣዊ መግለጫ ንግግር ያሰሙት የሥነ ቋንቋ ሊቅ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ፕሮፈሰር ክላውዲዮ ማግሪስ በተለያዩ ሃይማኖትች እና ከተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ጋር ለሚደረገው ውይይት መሠረት ነው በማለት፣ ቅዱስ አባታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ መሠረታው እና አበይት ሥነ ኅላዌ ጥያቄዎች የሰጠው መልስ መሆኑ በጥልቀ የሚያስረዳ እና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ ምን መሆኑ በማብራራት ያሰመሩትበት ሐሳብ አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርዕሰ አንቀጽ በመጥቀስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የሚያሳውቅ፣ ለአንዳንድ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ልጅ ድህነት የተሰዋ ሞት አሸንፎ የተነሣ ወደ አባቱ በመመለስም የሰው ልጅ ሕይወት አናሥር እና ፍጻሜ ለይቶ በሕይወት እና በቃል የገለጠ መሆኑ በጥልቅ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው በማለት ርዕሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.