2011-03-14 14:38:36

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ድጋፍ ለጃፓን ሕዝብ


በጃፓን በተከሰተው ርእደ መሬት እና ርእደ ባሕረ መሬት ሳቢያ ለተጠቃው ሕዝብ ድጋፍ የዓለም ሕዝብ እና መንግሥታት እጅግ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅድስት መንበር የተራድኦ ማኅበር RealAudioMP3 ጳጳሳዊ ውሁደ ልብ አምካኝነት ድጋፍ እና ትብብር ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበራትን በሚያቀፈው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በካሪታስ የሚጠራው የተራድኦ ማኅበር በኩል በርእደ መሬት እና በርእደ ምድረ ባህር እጅግ ለተጠቃው የጃፓን ሕዝብ ቁሳዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑ ሲገለጥ፣ የዚህ የተራድኦ ማኅበር የበጎ ፈቃድ አባላት በክልሉ በመገኘት ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ላይ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግልጫ ሲያመለክት፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፊርማ የሠፈረበት መልእክት አማካኝነት ቅዱስ አባታችን ለጃፓን ሕዝብ በጸሎት እንደሚያስቡዋቸው እና ቅርበታቸን ለማረጋገጥ ያስተላለፉት መልእክት በጃፓንኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በመላ ጃፓን በሚገኙት ሰበካዎች እና ቁምስናዎች በይፋ መነበቡ ተገለጠ። የጃፓን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በዖሳካ አስቸካይ ስብሰባ በመጥራት ለተጎዳው ሕዝብ ድጋፍ እና ትብብር ለማቅረብ የደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት በመገምገም የሚከተለውን ሥልት መቀየሱ በጃፓን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ አልበርቶ ቦታሪ ደ ካስተሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ፣ የርዕደ መሬት አደጋ እስከ ኦኪናዋ መዝለቁንም በማብራራት፣ በዚያ ክልል የደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት በውኑ ገና አልታወቀም ብለዋል። የተፈጥሮ አደጋው ክስስት በኋላ የደረሰው የሰው እና የንብረት እንዲሁም በተፈጥሮ ላይ ያስከተለው እና በጠቅላላ ጥሎት የሚያልፈው ዘርፈ ብዙ ችግር ግምት እየተሰጠ ነው ካሉ በኋላ፣ ቅድስት መንበር በጳጳሳዊ ውሁደ ልብ ማኅበር በኵል 150 ሺሕ ዶላር ለተጎዳው ሕዝብ መሠረታዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚውል ድጋፍ መሰጠቱንም ገልጠው፣ ይህ ድጋፍ በእውነቱ ከቅዱስ አባታችን የተሰጠ በመሆኑ መጽናናትን እና ብርታትን የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በጃፓን ወንጌላዊ ልኡክ በመሆን ማገልገል ከጀመሩ 38 ዓመት እያስቆጠሩ ያሉት ፍራንቸስካዊ ካህን አባ ክላውዲዮ ጃነሲን በበኩላቸውም 8.9 ሪኽተር ደረጃ የተለካው ርእደ መሬት ከፍተኛ የሰው እና የንብረት ጉዳት ማስከተሉ በመጥቀስ የተጎዳውን ህዝብ ለመደገፍ አቢያተ ክርስትያናት ቁምስናዎች ምእመናን በመተባበር ላይ መሆናቸው ገልጠው፣ የደረሰው ጉዳት በመለየት ድጋፍ ለማቅረብ በመከናወን ላይ ያለው ርብርቦሽ እጅግ የሚያስደንቅ ነው በማለት ከቫቲና ረድዮ ጋር ያካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.