2011-03-14 14:41:01

የቅዱሳት ምስክርነት፣ የክርስቶስ ኅላዌ የሚገልጥ ብልጭታ ነው


ከትላንትና እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ለበዓለ ፋሲካ ማዘጋጃ በቅድስት መንበር ቅዱስ አባታችን እና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ብፁዓን ካርዲናሎች እና ጳጳሳት የሚሳተፉበት የቀርመሎሳውያን ገዳማውያን ማኅበር አባል ፈረንሳዊ ካህን አባ ፍራንሱዋ ማሬይ ለዘል የቅዱሳት መስክርነት የክርቶስ ኅላዌ አመልካች ነው በሚል ርእስ የሚመራው ሱባኤ መጀመሩ ሲገለጥ፣ በተርሳኒዩም ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ RealAudioMP3 መምርህ አባ ፍራንሱዋ ማሪየ ለዘል “የክርስቶስ ብርሃን በቤተ ክርስትያን ማእከል፦ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና የሥነ ቅዱሳት ቲዮሎጊያ” በሚል ጠቅላይ ርእሰ የሚመራው እፊታችን ቅዳሜ የሚፈጸመው ሱባኤ ትላትና ከቀትር በኋላ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 12 ሰዓት በሐዋርያዊ መንበር መሚገኘው የመድሃኔ ዓለም እናት ቤተ ጸሎት መጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ክቡር አባ ፍራንሱዋ ማሬይ ለዘል ስለ ሱባኤው በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ሱባኤው እንድመራ እንደጠየቁኝ ጥያዌውን የጸሎት ርእስ አድርጌ በእግዚአብሔር ፈቃድ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እሺ በማለት፣ በእውነት የሱባኤው ርእሰ ጉዳይ ወደ በዓለ ትንሳኤ የሚሸኘን በተጨማሪም ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብፁዕ ወደ ሚባሉባት ቀን የሚመራን ነው። ይኽ ቅዱስ አባታችን የሰጡዋቸው ኃላፊነትም ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ለቅድስት ድንግል ማርያም በማቅረብ በዚህ መንፈሳው ድጋፍ ተበረታተው የሚፈጽሙት አገልግሎት መሆኑ ገልጠዋል።

ቅዱሳት የቤተ ክስትያን ቅድስና መስካሪያ ናቸው፣ የእነርሱ ቅድስናም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅላዌ ብልጭታ እና ኅያው ምስክርነት ነው፣ ይኽ ደግሞ እሳቸው የቅዱሳት ሥነ ቲዮሎጊያ ጉዳይ በተመለከተ ያካሄዱት እና እያካሄዱት ካለው ጥልቅ ጥንት እና ምርምር ጋር የሚያያዝ ነው። ስለዚህ መንፈሳዊው ሱባኤ፣ የተለያዩ ቅዱሳን መሠረት በማድረግ እና ከቤተ ክርስትያን መርህ ቃል እና ትምህርተ ሃይማኖት እና አንቀጸ ሃይማኖት ጋር በማጣመር ተከናውኖ በመጨረሻው የሱባኤው ቀን የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የጥምቀት ቅዱስ ሥም በሆነው በቅዱስ ዮሴፍ ቅድስና ላይ ያተኮረ እንደሚሆን አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.