2011-03-14 14:42:38

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ የቅ. አ. ር.ሊ.ጳ “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛ ተከታታይ መጽሓፍ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተከታታይ ባቀረቡዋቸው ኢየሱስ ናዝራዊ የተሰኙት ሁለት መጽሓቶቻቸው አማካኝነት የሰው ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ ለአንባብያን ተጨባጩን ኢየሱስ የሚያስተዋውቅ መሆኑ የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ሁለተኛው ተከታታይ መጽሓፍ በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ኢየሱስ ናዝራዊ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ RealAudioMP3 ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ለሚፈልግ ሁሉ የሚጠቅም “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛው መጽሐፍ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም መግባት ከሚለው ታሪክ በመጀመር፣ ሞቱን እና ትንሣኤው እንዲሁም ዕርገቱን በጥልቀት የሚያብራራ ነው ብለዋል።

ተጨባጩ የታሪኩ ኢየሱስ ላይ ቅዱስ አባታችን የሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት ወሳኝ ነው፣ አለ የታሪኩ ኢየሱስ የትንሣኤው የእምነት ክርስቶስን በሙላት ለመረዳትም ሆነ ለመቀበል ፈጽሞ የሚቻል አይደለም። ስለዚህ የታሪኩ ኢየሱስ ለመረዳት እጅግ አዳጋች በመሆኑም ቅዱስ አባታችን በዚሁ ጉዳይ ላይ ያተኮሩት አለ ምክንያት አይደለም፣ የታሪኩ ኢየሱስ በተመለከተ ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ ትንተና በማቅረብ የሰጡት የሐሳብ ጽማሬ የታሪክ ደረጃ እና የቲዮሎጊያ ደረጃ የሚያጣምር ነው። አነዚህ ሁለት ደረጃዎች ለያይቶ ማብራራት፣ በሁለቱ ደረጃዎች መካከል አለ መጣጣም አለ ማለት አይደለም፣ ተሟዮች ናቸው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን በደረሱት መጽሐፍ ይኸንን ሥልት፣ አብጠርጥረው በማስረዳት የክርስቶስ የሕይወት ታሪክ የክርስትና ታሪክ መሆኑም አሥምረውበታል።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት፣ ዘለዓለማዊነት፣ መለኮታዊ ባህርይ ፍጹምነት በታሪኩ ኢየሱስ ዘንድ ያለ መሆኑ የክርስትናው እምነት የእምነቱ ክርስቶስ እና የታሪክ ኢየሱስ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ሁኔታ እና ተጨባጭነትን የሚያስረዳ መጽሓፍ ነው። የእምነታችን እርገጠኝነት ወይንም እማኝነት የኢየሱስ ታሪክ ያስፈልገዋል። ሆኖም ይህ ታሪክ የታሪክ ሥነ ምርምር ማረጋገጫ ለመስጠት የሚከተለው ሥልት መሠረት የሚያደርግ አይደለም፣ ይህ ማለት ደግሞ የታሪክ ኢየሱስን ያገላል ማለት ሳይሆን፣ ከእምነት ተጨባጭ ሂደት ጋር የሚጻረር መሆኑ ለማስረዳት ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ግድፈት ለማንጻት መለኮታዊ ክብሩን ትቶ እራሱን ዝቅ በማድረግ የሁሉም አገልጋይ በመሆን በማንም የሃይማኖት ታሪክ ዘንድ የሌለ አዲስ እርሱም ልብን የሚያነጻ ሕግ እና ሥርዓት ሳይሆን እምነት መሆኑ የሚገልጥ አዲስ ሥር ነቀላዊ ለውጥ በቃል እና በሕይወት በማስተዋወቅ፣ አንዳንድ ነጻ የቅዱስ መጽሓፍ ተንታኞች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንጻት ሥርዓት በግብረ ገብ እንደ ተካው የሚናገሩት፣ ክርስትና መሠረታዊ ትርጉሙ እና መግለጫው ግብረ ገብ ነው እንደሚሉት እና አዲስ ሕግ ወይንም ደንብ ሳይሆን፣ የመንፈስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠው አዲስ ውስጣዊነት ነው። ክርስትና ጸጋ ነው። ጸጋ በመሆኑም እያደገ እና ከፍ ከፍ የሚል በተሰጠው ጸጋ መሠረት በንቃት የሚኖር እና የሚተገበርም መሆኑ ቅዱስ አባታችን በደርሱት መጽሓፍ በጥልቀት ያስረዳሉ።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት፣ የዓለም ኃጢአት ፍጹም ንጹሕ በሆነው ሰው እንደሚለወጥ ይኽም በፍጹም ፍቅር እና ስቃይ አማካኝነት በኃጢኣት ያደፈው ሰው እንደሚነጻ፣ መልካም ከክፋት እጅግ የላቀ እና ትልቅ መሆኑ ያረጋግጥልናል።







All the contents on this site are copyrighted ©.