2011-03-12 09:37:17

ግብጽ፦ የማኅበረ ክርስትያን ሕይወት


የርእሰ ብሔር ሆስኒ ሙባራክ ከሥልጣን መገለል አዲህ በግብጽ የሚታየው የመንግሥት የዳግመ ምዋቅራዊ ሂደት በተለያየ ሰላማዊ ሰልፍ እየተሸኘ መሆኑ ሲገለጥ፣ ከትላትና በስትያ የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ RealAudioMP3 የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጣሪ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ግብጻዊ ሞሃመድ ኤል ባራደይ ለርእሰ ብሔር ምርጫ እጩ ሆነው እንደሚቀርቡ ማሳወቃቸው ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በግብጽ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስት 14 ግብጻውያን ክርስያን ምእመናን ለሞት የዳረገው ማኅበራዊ ውጥረት እጅግ እንዳሳስበው ለማወቅ ሲቻል፣ በሙስሊሞች እና በኦርቶዶስክ ክርስትያኖች መካከል ያለው ውጥረት ገና እየቀጠለ ይነገራል።

ትላትና በተከሰተው ውጥረት ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡት 14 የኦርቶዶክ ሃይማኖ ምእመናን በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ዜጎች በተገኙበት የቅብር ሥነ ሥርዓት መፈጸሙ ሲገለጥ፣ የኮምቦናውያን ልኡካነ ወንጌል ማኅበር አባል አባ ጁዜፐ ስካቶሊን በግብጽ ስላለው ሁኔታ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በግብጽ የጥር 25 ቀን አብዮት በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ሕዝባዊ ንቅናቄ እያቀጣጠለው ያለው ለውጥ ባህላዊ ማኅብራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ አበክሮ የሚነካ መሆኑ ገልጠው፣ በአሁኑ ወቅት በሙስሊሞች እና በኦርቶዶክስ ክርስትያኖች መካከል የሚታየው ወጥረት በአገሪቱ ሁሉም ዜጋ አለ ሃይማኖት እና አለ ጎሳ ልዩነት እኵልነት የሚያረጋገጠው ከሃይማኖት ነጻ የሆነ መንግሥት እንዲረጋገጥ የሚያዘው የሕግ ሉአላዊነት በአገሪቱ ገና ሙሉ በሙሉ እግብር ላይ አለ መዋሉ የሚያረጋግጥ ሁኔታ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.