2011-03-12 09:34:47

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛ ተከታታይ መጽሓፍ


በቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ትላንትና በሁሉም ቤተ መጻሕፍት ለአንባቢያ የቀረበው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛ ተከታታይ መጽሐፍ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦውሌት፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ፕሮፈሶር ክላውዲዮ ማግሪስ እና የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ለንብባብ በቅቷል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ኢየሱስ ናዝራዊ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ ሁሉም RealAudioMP3 ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ለሚፈልግ የሚጠቅም መሆኑ ሲገለጥ፣ “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛው መጽሐፍ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም ንጉሥ መሆኑ የሚገልጠው ወደ ኢየሩሳሌም መግባት ከሚለው ታሪክ በመጀመር፣ እርሱም እንደ አንድ አብዮታዊ ፖለቲከኛ ጸረ ክርስቶስ በሆነው አመጽ ላይ የተመሠረተ እንዳልሆነ ከሚገልጠው ታሪክ በመንደርደር ቅዱስ አባታችን፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሥነ ፍጻሜ የሚገልጥ ንግግር በማስቀደም ስለ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መፈራረስ እንዲሁም ስለ ፍርድ ቀን እና የዓለም ፍጻሜ በመናገር፣ “እግዚአብሔር የታሪክ ጌታ የሆነው ለሰው ልጅ የሰጠው ነጻነት ትርጉም እና ኢየሱስ እውነተኛ መቅደስ የድንጋዩ ቤተ መቅደስ መቀደሙን የመሰከረ ገዛ እራሱ እውነተኛ እና አዲስ ቤተ መቀደስ መሆኑና በእርሱ አመካኝነትም እግዚአብሔር እና ዓለም እንደሚያገናኝ አብራርተው።

ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ግድፈት ለማንጻት መለኮታዊ ክብሩን ትቶ እራሱን ዝቅ በማድረግ የሁሉም አገልጋይ በመሆን በማንም የሃይማኖት ታሪክ ዘንድ የሌለ አዲስ እርሱም ልብን የሚያነጻ ሕግ እና ሥርዓት ሳይሆን እምነት መሆኑ የሚገልጥ አዲስ ሥር ነቀላዊ ለውጥ በቃል እን በሕይወት በማስተዋወቅ፣ አንዳንድ ነጻ የቅዱስ መጽሓፍ ተንታኞች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንጻት ሥርዓት በግብረ ገብ እንደ ተካው ይናገራሉ፣ እንዲህ ቢሆን ኖር ክርስትና መሠረታዊ ትርጉሙ እና መግለጫው ግብረ ገብ ሆነ በቀረበ ነበር። ስለዚህ አዲስ ሕግ፣ አንድ አዲስ ሕግ ወይንም ደንብ ሳይሆን የመንፈስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠው አዲስ ውስጣዊነት ነው። ክርስትና ጸጋ ነው። ጸጋ በመሆኑም እያደገ እና ከፍ ከፍ የሚል በተሰጠው ጸጋ መሠረት በንቃት የሚኖር እና የሚተገበርም መሆኑ ቅዱስ አባታችን በደርሱት መጽሓፍ በጥልቀት ያስረዳሉ።

በመቀጠልም ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ስለ ይሁዳ ሲተነትኑ፣ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች ያንን የተሰጠንን ጸጋ በሁለት ዓይነት መንገድ ለመኖር እና እግብር ላይ ለማዋል እንደሚቻል የሚያመለክት እርሱም ሁለቱም ጸጋውን ተቀብለዋል። ጴጥሮስ ክርስቶስን ክዶ ሲያበቃ ነገር ግን በእውነት በመጸጸት በምኅረተ ላይ ያለው እምነት ይመሰክራል፣ ይሁዳ ምንም’ኳ በፈጸመው ግብረ ክህንደት ቢጸጸትም ነገር ግን በምኅረት ላይ እምነት የሌለው በመሆኑ ጸጸቱ ተስፋ ቢስነት ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ የቤተ ክርስትያን እና የቅዱሳት ምሥጢራት ተካፋይ ማኅበረሰብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም የሚቀበሉ ናቸው። ሆኖም ስንቱ ነው ይኸንን ምሥጢር ቢቀበልም ሲክደው የሚታየው።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካህነታዊ ጸሎት፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ የዓለምን ኃጢአት የሚያነጻ በመሆን የመላ ታሪክ ትርጉም እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር መታርቅ የሚለው መሠረት ያደረገ መሆኑ ያረጋግጣል።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻው ማዕድ፣ በሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላውያን እና እንዲሁም በዮሓንስ ወንጌል ጭምር፣ በተለይ ደግሞ በዮሓንስ ወንጌል የመጨረሻ የእራት ማዕድ፣ ከፋሲካ ዋዜማ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተፈጸመ ሲሆን፣ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው በፋሲካ ቀን ሳይሆን በፋሲካ ዋዜማ ቀን መሆኑ ይገልጣል። ስለዚህ እወነተኛ የእግዚአብሔር በግ መሆኑ በመግለጥ የፋሲካ እውነተኛ ትርጉሙ እራሱን አሳልፎ በመስጠት ይገልጣል።

በጌተሰማንየ በእግዚአብሔር ፈቃድ እራሱን አሳምኖ እንዳተ ፈቃድ በማለት ሓጢኣት የሌለው ሆኖ በሓጢኣት ድቅድቁን ጭለማ በማለፈ እና በራሱ ላይ በማኖር መስቀልን ተሸከመ። ሆኖም ጌታችን መስቀል እንዳይሸከም ጴጥሮስ ያሳየው ጥረት ብዙውን ግዜ በክርስትያኖች እንዳውም አንዳንዴ ቤተ ክርስትያንም ሳትቀር የሚያጋጥማት ፈተና ነው። ስለዚህ ይህ የማንቀላፋቱ ጉዳይ እንዳያጋጥም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚለው መንቃትን ይጠይቃል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እፍርድ ፊት መቀረብ፦ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተበየነው የሞት ፍርድ ተጠያቂ አይሁዳውያን እንዳልሆኑ ቅዱስነታቸው በማስረዳት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ደቀ መዛሙርቱ ጭምር አይሁዳውያን እንደነበሩ ያስገነዝባሉ። ስለዚህ ጌታችን ለሞት ፍርድ አፍሳልፎ በመስጠት ተጠያቂው የወቅቱ ልኡላዊ አምባገነ ሥርዓት ነው ብለዋል።

ጲላጦስ፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተከፈተውን ችሎት ሲመራ፣ እውነት ምን ማለት ነው ሲል ጥያቄ ያቀርባል፣ ብዙዎችም ይከንን መሠረት በማድረግ እውነት ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ እስካሁን ድረስ ገና መልስ ያላገኝ ክፍት ጥያቄ ወይንም ያልተፈታ ጥያቄ ነው ብለው ይናገራሉ፣ ቅዱስ አባታችን በዚህ በተነተኑት ሀሳብ ላይ በማከል ሆኖም ግን ማንኛውም ሰው አለ እውነት የሕይወትን ትርጉም ሊቀበልም ሊያስተናግድም ሊረዳም አይችልም፣ እውነት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን፣ እውነት ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ስቅለት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እያለ በቅድሚያ የሚያደርጉትን አያውቁም በማለት ምንም’ኳ አለ ማወቅ የልብ ማደንደንን ወይንም የተለያዩ የእውቅት ዘርፎች ባለ ቤትነትን እና ግኡዛዊ እውቀትን የሚያመለክት ቢሆም ቅሉ አክሎም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያደርጉት አያውቁም በማለት ለአባቱ የተናገረው ቃል ለሁሉም ሰው ልጅ እና ታሪክ ማጽናኛ ነው።

ጌታችን በተሰቀለበት መስቀል በስተቀኝ በኩል የተሰቀለው ወንጀለኛ፣ የእግዚአብሔር ምኅረት በመጨረሻ ሰዓት ለመቀበል እንደሚቻል ያረጋግጥልናል።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት፣ የዓለም ኃጢአት ፍጹም ንጹሕ በሆነው ሰው እንደሚለወጥ ይኽም በፍጹም ፍቅር እና ስቃይ አማካኝነት በኃጢኣት ያደፈው ሰው እንደሚነጻ፣ መልካም ከክፋት እጅግ የላቀ እና ትልቅ መሆኑ ያረጋግጥልናል።

ትንሳኤ፣ አለ የትንሳኤ እምነት የክርስትና ባዶ ትርጉም አልቦ ነው። የጌታችን ክርስቶስ ትንሳኤ ዳግም ሕይወት የዘራ ሬሳ ማለት ሳይሆን ሞትን ፈጽሞ የደለዝ ወሳኝ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት፣ ለሰው ልጅ አዲስ መጪ ሕይወት የሚያረጋገጥ ነው። ትንሳኤ በሥነ ምርምር የሚደገፍ እውነት የሚያስቀምጥ ሳይሆን፣ ከሥነ ምርምር ጋር የማይጻረር እርሱም የሰው ልጅ በውስጡ የሚያስተነትነው መሆናዊ ዝንባሌ ነው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳልፈው ለሰጡት ሳይሆን ለአንዳንድ ሰዎች ብቻ ለምን ተገለጠ የሚለው ጥያቄ ቅዱስ አባታችን ሲያድረዱ፣ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ታሪክ ታሪክን ሲሰራ የሰው ልጅ እንደሚያደርገው ትምክህተኝነት የሚያጎላ ሳይሆን ዝቅ ብሎ ትሁት እና ቀስ በቀስ የሚሠራ እና ዘወትር በያንዳንዱ ልብ የሚያንኳኳ በሩን ለሚከፍትለት እንዲያዩት የሚፈቅድ መሆኑ የሚያረጋጥ እውነት ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በመጽሓፉ ማጠቃለያ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ መነሳቱ የተረጋገጥ ነው። እናምናለንም ምንም’ኳ ፍርሃት የሚከተለን ማዕበል የሚያናውጠን ቢሆንም በዓለም ፍጻሜ ዳግም በክብር እንደሚመጣ በእርሱ ላይ ያለን እማኔ ከለላችን ደስታችን ነው የሚለውን ጥልቅ ሀሳብ ምእከል በማረግ ዕርገት ምን ማለት መሆኑ ይተነትናሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.