2011-03-12 09:36:08

ቅዱስ አባታችን፣ ዓለም ወደ እግዚአብሔር ዳግም መመለስ ያስፍልገዋል


ከትላትና በስትያ የላቲን ሥርዓት ግጽዊ የምክትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዓቢይ ጾም በይፋ የጀመረችበት ዕለት መሆኑ ሲገለጥ፣ ለዓቢይ ጾም የመግቢያ ሥርዓት ስታዚዮ ኳረዚማለ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ማኅበረ ክርስትያን እና መንፈሳውያን ነጋድያን በጋራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል እና እርሱን ለመመስከር ቃል የሚገቡበት ብሎም የእምነት ሰማዕት የሆኑትን ቅዱሳት RealAudioMP3 አማካኝነት ጸሎት በማሳረግ የአመድ መባረክ እና በራስ ላይ በመነስነስ ንስሃ፣ መለወጥ ማእከል ያደረገ የሊጡርጊያ ሥርዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ በሚግኘው በቅድስ ሳቢና ባዚሊካ በቅርብ ተባባሪዎቻችው ብፁዓን ካርዲናሎች እና ብፁዓን ጳጳሳት ጋር በመሆን ሥርዓተ ቅዳሴ በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ ሁሉም በእውነት እንዲለወጥ እና እውነተኛ መለወጥ እንዲኖር እና ቅድስናውን ኃይሉን ክብሩን በማወቅ ወደ እግዚአብሔርም እንዲመለስ ጥሪ በማቅረብ፣ ዓለማችን ወደ የእግዚአብሔር መመለስ እንደሚያስፈልገው ገልጠው፣ መለወጥ ተቻይ የሚያደርገው እግዚአብሔር ምኅረቱ እና ፍቅሩ ታላቅ ነው ብለዋል።

በወንጌላዊ ምስክርነትም እኛ ክርስትያኖች ኅያው ምስክሮች እንዳውም አንዳንዴ በተለያየ ቦታ ለሚገኙት የኅብረሰብ ክፍል ብቸኞች ወንጌል ሆነን ልንገኝ እንችላለን፣ ስለዚህ የወንጌል ኅያው ምስክሮች ለምሆን ተጠርተናል ካሉ በኋላ በዚህ አቢይ ጾም ምጽዋት ጸሎት እና ጾም እግዚኢብሔር የልባችን ጥልቅ ሃሳብ በጥልቀት የሚያውቅ መሆኑ በሚያረጋገጥ እማኔነት ተመርቶ እነዚህ በዓለ ትንሳኤ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት በምናደርገው ጉዞ የሚሸኑን ቅዱሳት ተግባሮችን በመፈጸም እራሳችንን ለበዓለ ፋሲካ እናዘጋጅ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.