2011-03-11 17:23:57

ርሊጳ በነዲክቶስ ከየሮማ ሀገረ ስብከት ቁምስናዎች ካህናት ተገናኙ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሮማ ሀገረ ስብከት ቁምስናዎች ካህናትን ቫቲካን ላይ ተቀብለው አነጋግረዋል ።

ቅድስነታቸው በዓመት አንድ ግዜ ከይሮማ ሀገር ስብከት ካህናት እንደሚገናኙ የሚታወስ ሲሆን ፡ ካህናቱ ከቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር የተገናኙት በሮማ የቅድስነታቸው ሐዋርያዊ ወኪል ብብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ መሪነት እንደሆነ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።

ቅድስነታቸው ከሮማ ሀገር ስብከት ቁምስናዎች ካናት እንደተገናኙ ለካህናቱ ባደረጉት ንግግር የእግዚአብሔር ልብ ያላችሁ ሰዎች ናችሁ የእግዚአብሔር ሐቅን ዘወትር መስበክ አለባችሁ ክሁሉም በላይ ግን ድሆችን ውደዱ ብለዋቸዋል።

በነዲቶስ አስራ ስድስተኛ በማያያዝ ካህን አስተዳዳሪ አይደልም ፡ ኢየሱስ ክርስቶን ለመምሰል በእግዚአብሔር የተመረጠ ነው ትህትና ያለው የሰው ዘር የሚወድ ቤተ ክርስትያንን ከልብ የሚያገለግል ነው ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ሐውርያት የክርስቶስን ትምህርት ለዓለም እንዳዳረሱ ሁሉ ካህናት የነሱ ዱካ ተከትለው የቤተ ክርስትያን ትምህርት የሚያሰራጩ ለእግዚአብሔር ያደሩ መሆን እንደሚጠበቃባቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከየሮማ ሀገር ስብከት ቁምስናዎች ካህናት በተገናኙበት ግዜ ማሳሰባቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጭ አስገንዘበዋል።

ካህን የእምነት ጌታ አለመሆኑ እና በሙሉ ኃይሉ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆነ እና በዚሁ ዘመናዊ ዓለምም ቢሆን ካህን የክርስቶስ ሐዋርያት የሄዱበትን መንንገድ የሚሄድ መሆኑ ከክርስቶስ መሆን ከሱ ጋር መራመድ እሱን መምሰል የክርስቶስ አምባሳደር በምድር መሆኑ ከቶ መዘንጋት እንደሌለበት ቅድስነታቸው አጽንኦት ሰጥተው ለካህናቱ እንደገለጡላቸው መግለጫው አክሎ ዘግበዋል።

በአጠቃላይ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ካህናት በትህትና ግን በቁራጥነትን እና በመተማመን ቃለ እግዚአብሔርን ማሰራጨት እንዳለባቸው ጠቅሰው ዋነኛ ተልእኮ እሱ ነው እና ብለዋል በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ።

ካህናት በስብከት ግዜ ለነሱ እንደሚመስላቸው እና ለነሱ ደስ የሚላቸውን አይደለም መስበክ ያለባቸው ይልቁንስ ስብከቱ ጥልቅ ትምህርተ ቅዱስ ውንጌል ትኩረት የሰጠ መሆን እንዳለበት የእግዚአብሔር ፍላጎት የሚያሟላ እና መለኮታዊ ተግባርን ያነጣጠረ ለህዝበ ክርስትያን መንገር ማስረዳት መግለጽ እና ማብራራት እንጂ ብለውል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ።

በዚች ዓለም ላይ የሚጨበጡ እና የማይጨበጡ ነገራ ሲተረኩ ሲወሩ ሲዘረዘሩ በሚታይበት ግዜ የቤተ ክርስትያን ዋነኛ ዓላማ የእግዚአብሔር ህልውና ለህዝብ ክርስትያን እና ኢ ክርስትያን መንገር ዓለማዊ የሆኑ ነገራት ሁሉም ሐላፊዎች መሆናቸው ዘለዓለማዊ ሕይወት መኖሩ ፈሪሐ እግዚአብሔር እንዲኖር ግብረ ገብነት እንዲያብብ መሆኑም ጨምረው መግለጣቸው የቅድስነታቸው እና የሮማ ሀገር ስብከት ቁምስናዎች ካህናት ግንኙነት የተከታተለ የቫቲካን የዜና ወኪል አመልክተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዘለዓለማዊት ሮማ ጳጳስ መሆናቸው እና በዓመት አንድ ግዜ ከሀገር ስብከቱ ቁምስናዎች ካህናት እንደሚገናኙ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ ትናትና

ቫቲካን ላይ የተካሄደው ግንኙነት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ለሮማውያን ካህናት ሲናገሩ ፡ ካህን ራሱ መጠበቅ ተገቢ ቢሆንም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ክርስቶስ ለመምሰል ሕይወቱ አስላፎ ለመስጠትም ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል።

በማያያዝ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ የካህን ጥሪ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥሪ እንጂ የስራ ሙያ አለመሆኑ እና የእግዚአብሔር ምርጫ እንደሆነ አስምረውበታል።

ካህናት መንፈሳውያን ድንግል እና ንጹሐን ሆነው ትህትና ማዘውተር የሚያደርጉት የሚሉት እና የሚያስቡት ህሉ ክርስቶስን የተለከተ ካልሆነ ታድያ መለኮታዊ ጥሪ እና ተልእኮ ሊሰናከል እንደሚችልም አሳስበዋል።

ከካህናት የሚጠበቀው መንፈሳውያን እረኞች መሆን ሁለንትናቸው ለከሀሌ ኩሉ ለእግዚአብሔር የሚሰጡ ሲሆኑ መልካም እና የሚያምር የሚያስደት ይሆናል ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ካህናት ከክርስቶስ ጋር ጥብቅ ግንኙነት እና ዝምድና ከሌላቸው በምን ዓይነት መንገድ ሀዝብ ክርስትያንን ከፈጣሪ ጋር ሊያገናኙት ይችላሉ ማለታቸው ከቫቲካን የወጣ መግለጫ አመልክተዋል።

ፍቅር ከጥላቻ ያይላል እግዚአብሔር ከተጻራሪው ሁሉ በበለጠ ኀይለኛ መሆኑ በመገንዘብ ቤተ ክርስትያን የሚገትምዋት ችግሮች ሁሉ በኃየለ መስቀሉ ድል ትሆናለች እኛም ሁሌ በጸሎት በአስተንትኖ እንሰኛት በማለት አክለው መገለጣቸው ተገልጸዋል።

የሮማ ሀገር ሰብከት ቁምስናዎች ካህናት መርተው ከበነዲክቶስ ጋር የቀረቡ በሮማ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ ቅድስነታቸው ለካህናቱ ያደረጉት ንግግር በልብ አመስግነው ዛሬ በቅድስት መንበር ማኅተም ክፍል ይፋ የሆነውን በነዲክቶስ የደረሱት ክርስቶስ ናዝራዊ የተሰየመ ሁለተኛ እትም ለአርባ ጾም መልካም ጓደና መሆኑ ገልጸውላቸውል ፡ በዚህም በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና ሮማውያን ካህናት መካከል የተደረገውን ግንኙነት ፍጻሜ ሁነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.