2011-03-09 16:08:47

ጳጳሳዊ ዓመታዊ የዘገባ ሰነድ


ሐዋርያዊ የግጽዊ ጽሕፈት ቤት የ 2011 ዓ.ም. የቤተ ክርስትያን ጠቅላላ ሂደት በአኃዝ በማስደገፍ ያቀረበው ገምጋሚ ሰነድ፣ ሓዋርያዊ የቤተ ክርስትያን ግጽዊ ማእከል ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ቪቶሪዮ ፎርመንቲ እና የዚህ ሐዋርያዊ የቤተ ክርስትያን ግጽዊ ማእከል የሥነ ግጽዊ ሊቅ ፕሮፈሰር ኤንሪኮ ኔና የጥናቱን ዓመታዊ ሰነድ በይፋ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር RealAudioMP3 መግለጫ አሳውቆ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸንን ዓመታዊ የቤተ ክርስትያን ሁኔታ ዘጋቢ ሰነድ በማስደገፍ ብፁዕ አቡነ ፎርመንቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የጥናቱ ሰነድ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የካህናት ጥሪ ከፍ እያለ መምጣቱ እና እድገቱም አወንታዊ መሆኑ እንደሚያመለክት ጠቅሰው፣ ስለዚህ የካህናት የልኡካነ ወንጌል የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በጠቅላላ ከፍ እንዳለ ከሚያረጋገጠው አኃዝ በስተጀርባ የተጠሪው ሰው ጉዳይ የሚመለከት እና ይኽ ማለት ደግሞ የካህናቱ ተልእኮ አገልግሎት በጠቅላላ የቤተ ክርስትይን የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ሂደት የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል።

የጥሪ ከፍ ማለት የሚያስደስት ቢሆንም፣ ተፈላጊው በቁርጥ ብዛት ማደግ ሳይሆን የሚሰጠው አገልግልት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የካህናት ጥሪ ከፍ ማለቱ እንዳስደሰታቸው እና ይኽ ደግሞ ለምስጋና ጸሎት ርእሰ ጉዳይ መሆን እንዳለበት ማሳሰባቸው ብፁዕ አቡነ ፎርመንቲ ዘክረው፣ እ.ኤ.አ. ከ 60 ዓመታት እስከ ባለፈው ዘመን ፍጻሜ ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የካህናት ቁጥር ዝቅ እያለ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፣ ሆኖም ግን ከ 1998 ዓ.ም. ወዲህ ምንም’ኳ የእድገቱ መሥፍርት በቁጥር አንጻር ሲታይ እድገቱ እጅግ ከፍ ያለ ባይሆንም ከዚህ ከተጠቀሰው ዓመት ወዲህ የጥሪ ብዛት ቁጥር ከፍ እያለ እና ቀጣይ እየሆነ መምጣቱ የሚያረጋገጥ ነው። የካህናት ብዛት ከፍ ማለት ከ 2000 ዓ.ም. ወዲህ ሲታይ የሚያስደስት የካህናት ዓመት በታሰበበት ወቅት በዓለም ደረጃ 1.400 የዘርአ ክሀነት ተማሪዎች ምሥጢረ ክህነት መቀበላቸው እና ሌሎች 460 በተለያየ ምክንያት በቤተ ክርስትያን ውሳኔ መሠረት ከክህነት አገልግሎት ተገለው የነበሩት፣ ዳግም የክህነት አገልግሎታቸው እንዲፈጽሙ ፈቃድ ማግኘታቸው ጠቅሰው፣ በጠቅላላ ቅዱስ አባታችን የዓመቱ ሰነድ ያስቀመጠው አወንታዊ መግለጫ ደስ እንዳሰኛቸው ብፁዕ አቡነ ፎርመንቲ ገልጠዋል።

ለምሳሌ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ በተሾሙበት ዓመት በዓለም የዓቢይ ዘረአ ክህነት ተማሪዎች ብዛት 69 ሺሕ እንደነበር እና በ 2009 ዓ.ም. የዓቢይ ዘረአ ክህነት ተማሪዎች ብዛት ወደ 117 ሺሕ ከፍ ማለቱ ብፁዕነታቸው በመግለጥ፣ በክፍለ ዓለም ደረጃ ሲታይ በኤውሮጳ ያለው ሁኔታ ዝቅ ያለ መሆኑ እና በጠቅላላ በሰሜን እና በደቡብ አመሪካ የካህናት ጥሪ ከፍ እያለ ሲሆን በእስያ የካቶሊክ ሃይማኖት ምእመናን ውሁዳን ቢሆኑም ቅሉ የካህናት ጥሪ ጽኑ እና በሕንጸት ረገድም የሚደነቅ ነው። በአፍሪካ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ብዛት ከፍ እያለ ቢሆም ነገር ግን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት የሚከታተሉ የሕንጸት ካህናት እጥረት እንዳለ በመግለጥ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.