2011-03-09 16:05:55

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን


እ.ኤ.አ መጋቢት 8 ቀን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታስቦ የሚውልበት ዕለት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ትላትና በተለያዩ የዓለምችን ክፍሎች የሴቶች ተሳትፎ በፖለቲካው በማኅበራዊ እና በኤኮኖሚው ጉዳይ ላይ ባተኮሩ መርሃ ግብሮች ተሸኝቶ ታስቦ ውሎኣል። ዓለም አቀፍ የእርሻ እና የምግብ ድርጅት እኩልነት የላቀ እና ክቡር ዓላማ ብቻ ሳይሆን ለተሟላ እድገት እና RealAudioMP3 በምግብ እራስን መቻል የሚለው ዓላማ ለማረጋገጥ ውሳኝ መሆኑ ቀኑን ምክንያት በማድረግ እራሃብ ጨርሶ ለማስወገድ ለሚደረገው ትግል የሴቶች ተሳትፎ መሠረት ነው በሚል ርእስ ሥር ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ዣክ ዲዩፍ ካሠፈሩት ሃሳብ ለመረዳት ሲቻል፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች ማኅበራዊ ሰብአዊ ኤክኖሚያዊ እድገት የሚያነቃቃው መንግሥታዊ ያልሆነ ፓንገአ የተሰየመው የግብረ ሰናይ ማኅበር እቅድ አስፍፈጻሚ ጉዳይ ተጠሪ ሲሞና ላንዞኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዓለማችን በድኽነት ጫንቃ ሥር ከሚገኘው ከጠቅላላው ሕዝብ ብዛት ውስጥ ሴቶች 70% እንደሚሸፉኑ መሆናቸው እና ቤተሰብ ለመመገብ በሚደረገው ጥረት ተቀዳሚው ሚና የሚጫወቱም ሰቶች ሆነው እያሉ፣ ሆኖም ግን በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከተጠቁት የኅብረተሰብ ክፍል ከፍተኛውን ቁጥር የሚሸፍኑ ናቸው። ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባት ይህ የግብረ ሰናይ ማኅበር በሁሉም መሥክ የሴቶች እኩልነት ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ ልማት አለ ሴቶች ተሳትፎ እንደማይሳካ ገልጠው፣ ስለዚህ በሴቶች ላይ እያንዣበበ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር መቅረፍ እርሱም በሴቶች ላይ የሚፈጸመ አድልዎ፣ ዓመጽ ወዘተረፈ ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት ለዓለማችን የበለጠ እድገት መሠረት ነው በማለት የሰጡን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.