2011-03-09 16:04:32

ሁለተኛው የቫቲና ጉባኤ፦ ኦፕታታም ቶቲዩስ፣ ስለ ካህናት ሕንጸት ጉዳይ የሚመለከተው ውሳኔ


የእየሱሳውያን ማኅበር አባል የቲዮሎጊያ እና የስነ ቅዱሳት ጉባኤዎች ሊቅ አባ ዳሪዩስ ኮዋልዝይክ በቫቲካን ረዲዮ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ማእከል በማድረግ የጀመሩት የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላትና የካህናት ሕንጸት ጉዳይ የሚመለከተው ኦፕታታም ቶቲዩስ የተሰየመው ውሳኔ በማደገፍ ሲያድረዱ፣ አለ የዘርአ ክህነት ተማሪ የካህናት ሕንጸት ብሎ ለመናገርም ሆነ ለማሰብም የማይቻል ነው። RealAudioMP3 ስለዚህ ይኸንን በመረዳት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በዚህ ኦፕታታም ቶቲዩስ የተሰየመው ውሳኔው አማካኝነት የክህነት ጥሪ የሚያነቃቃው ማኅበረ ክርስትያን መሆኑ ማእከል በማድረግ፣ ይህም ቀዳሚ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ተብላ ከምትገለጠው ቤተሰብ የሚጀምር መሆኑ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ ያመለክታል። ስለዚህ የክህነት ጥሪ ኅያው እምነት ካለባት ቤተሰብ እና ማኅበረ ክርስትያን የሚጀምር ነው ብለዋል።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በዚህ የካህናት ሕንጸት ጉዳይ የሚመለከተው ውሳኔ በአምስት አድማሶች ሥር፣ በቅድሚያ መንፈሳዊ አድማስ፣ አዕምሮአዊ ሕንጸት ሥነ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እና በተለያዩ የዓውደ እውቀት ሕንጸት እና በመጨረሻም የሰብአዊ ሕንጸት በተሰየሙት የሕንጸት ዘርፎች ሥር በማብራራት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረው ግኑኝነት በሰብአዊ ብስለት እድገት የሚሸኝ መሆን እንዳለበት ያሳስባል። ስለዚህ በጠቅላላ የሕንጸቱን አድማስ የቤተ ክርስታያን ሥልጣን በተለያዩ ካህናት አማካኝነት የሚኖረው ኃላፊነት ለመቀበል እና ለመታዘዝ ዝግጁዎች ለማድረግ የሚያግዝ መሆን አለበት።

የዓውደ እውቀት ሕንጸት ካህናት፣ ለተለያዩ ችግሮች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ብርሃን ላይ የጸና መልስ ለማቅረብ እንዲችሉ፣ ዘለዓለማዊ እውነትን በዚህ በሚለዋወጠው ዓለም እግብር ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆን አለበት። እንዲሁም ካህን ከሥነ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በሚያገኘው ሕንጸት አማካኝነት ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ የሚለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥሪ የሚኖር እንዲሆን ማገዝ ማለት መሆኑ አባ ኮዋልዝይክ በማብራራት፣ ኢአማንያን ወደ ሆኑት ለመቅረብ እና ስለ ድኅነት ለነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል የሚመሰክር ነው። ስለዚህ ለዚህ ተልእኮ የሚደገፈው የዓወደ እውቀት ሕንጸት ማግኘት ይኖርበታል ካሉ በኋላ፣ ይህ ሕንጸት ለዘረአ ክህነት ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን የክህነት ምሥጢር ለተቀበሉት ጭምር እንደ አስፈላጊነቱ ቀጣይነት ባለው መልክ መቅረብ እንዳለበት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የካህናት ሕንጸት ጉዳይ ውሳኔ ያመለክታል ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.