2011-03-07 16:02:24

የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ፦ ክርስትና እና ምስልምና


የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ትላትና ክርስትያን ምእመን እና የእስልምና ሃይማኖት ምእመን ርእሰ ጉዳይ በማድረግ፣ በፓኪስታን የተገደሉት በአገሪቱ የመንግሥት ሥልጣን በኃላፊነት የተቀመጡት ብቸኛ የመጀመሪያ ካቶሊክ ምእመን የአገሪቱ የውሁዳን የኅብረተሰብ ጉዳይ ሚኒ. ሻባዝ ብሃቲ እና እንዲሁም በፓኪስታን ብዙ የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮ ለሞት አደጋ እያጋለጠ ያለው የእግዚአብሔር ስም ማርከስ RealAudioMP3 በሌላ መልኩ የምስልምና ሃይማኖት ማርከስ ከሚለው ጋር በማያያዝ ለሞት አሳልፎ የሚያሰጥ ወንጀል ነው የሚለው በአገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ዘንድ ሠፍሮ ያለው አንቀጽ በተለያየ ወቅት በመቃወማቸው ምክንያት በአክራሪያን ሙስሊሞች ለሞት የተዳረጉት በአገሪቱ የፑንጃብ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሳልማን ታሲር ርእሰ ጉዳይ በማድረግ፣ ሁለቱ በፅንፈኞች ሙስሊሞች እጅ ለሞት የተዳረጉት አንዱ ክርስትያን አንዱ ደግሞ የምስልምና እምነት ተከታዮች ቢሆንም የተገደሉበት ምክንያት አንድ እና ተመሳሳይ ነው። እርሱም በፓኪስታን በወጀለኛ መቅጫ ሕግ ዘንድ ሠፍሮ ያለው ሃይማኖትን እና እግዚአብሔርን ማርከስ ለሞት ፍርድ የሚያሰጥ ነው የሚለውን አንቀጽ በመቃወማቸው ነው። እርሱም የእግዚአብሔር ስም ለኢፍትኅዊነት እና ለሞት ፍርድ ፈጽሞ ምክንያት ሊሆን አይችልም በማለታቸው ለሞት መዳረጋቸው አባ ሎምባርዲ በማብራራት፣ በአገሪቱ የሃይማኖት እና የውሁዳን ክፍለ ኅብረተሰብ ነጻነት እና ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲከበር ያቀርቡት በነበረው ጥሪ አማካኝነት በአክራሪያን እጅ ሊገደሉ እንደሚችሉ ቀድመው ያልዘነጉት ጉዳይ ቢሆንም ነገር ግን ለዚህ ቅን እና ለላቀው ዓላማ መቆም የላቀ ክብር መሆኑ በማመን እራሳቸውን ለሞት አደጋ በማጋለጥ ይኸው መሥዋዕት ሆነዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ጥር ወር የታሲር መገደል እንዳሳዘናቸው እና የእኚህ የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሞት ለሃይማኖት ነጻነት መከበር የሚያነቃቃ ይሆን ዘንድ የከፈሉት የሕይወት መሥዋዕት ባክኖ እንደማይቀር ነው ማለታቸው አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ አክለውም ሚኒስትር ብሃቲ ፓኪስታን ከፅንፈኞች እና ከማንኛውም ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ የአክራሪነት ርዕዮተ ዓለም ነጻ ትሆን ዘንድ ካለ መታከት እንደሚጥሩ እና ሁሉም በጸሎት እንዲደግፉዋቸው አደራ ብለውም እንደነበር አባ ሎምባርዲ ዘክረው፣ ሆኖም በሳቸው ላይ የተጣለው የሞት አደጋ፣ በርግጥ በፓኪስታን የማኅበረ ክርስትያን ሕይወት እጅግ ምንኛ ለአደጋ የተጋለጠ መሆኑ የሚያረጋገጥ እና ሁለቱ በእምነት የተለያዩ የአገሪቱ ዜጎች የከፈሉት የደም መሥዋዕት በአገሪቱ ለማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ሰላም እንዲሁም ለጋራው ውይይት እና ፍትህ መሠረት እንዲሆን እና እግዚአብሔር ወይንም ሃይማኖት የሕይወት እና የሰላም መሠረት እንጂ የሞት እና የሁከት ምክንያት አይደለም በማለት ያቀረቡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.