2011-03-07 15:59:17

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ እንደ ኢየሱስ መኖር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሮማ የአቢይ ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ጠባቂት ቅድስት ድንግል ማርያም የእምነት ቅዱስት እመቤት በዓል ምክንያት ባለፈው ዓርብ በሮማ ሰበካ አቢይ የዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ የአቢይ ዘረአ ክህነት እና የንኡስ ዘርአ ክህነት ተማሪዎች እና አለቆች የተሳተፉበት ለበዓሉ ምክንያት ያረገው አንደኛ RealAudioMP3 የሠርክ ጸሎት በመምራት ሥልጣናዊ መለኮታዊ ንባበ ትምህርት መስጠታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው በሰጡት ሥልጣናዊ መለኮታዊ ንባበ ትምህርት፣ የቤተ ክርስያን ውህደት ከውጭ ኃይል ወይንም አካል ተጽዕኖ የሚለደብ መለያ ሳይሆን በጋራ እና በሚስማማ እንደ ኢየሱስ በእርሱ የመንፈስ ኃይል አማካኝነት በመመራት ከሚኖር ሕይወት የሚመነጭ መሆኑ በማሳሰብ፣ ክርስትያናዊ ፍቅር ነጻ የሚያወጣ ትእዛዝ መሆኑ ገልጠው። ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልሞን በጻፈው መልእክት መግቢያ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ ከሆነው ሲል ገዛ እራሱን የክርስቶስ ምርኮኛ እንደሆነ አድርጎ በመግለጥ ያለውን ቃል መሠረት በማድረግ ካብራሩ በኋላ እያንዳንዳችን በዚህ ለክርስቶስ ካለን ነጻ የሚያወጣ ተግገዥነት ከሌሎች እና ከእግዚአብሔር ጋር ራሳችንን እናጣምራለን፣ ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛ አገልጋይ በመሆን እራሱን ዝቅ በማድረግ በገለጠው ፍቅር አርአያ በመከተል እጆቻችንን እና ልባችንን የዚህ ፍቅር ተገዥ ማድረግ ይኖርብናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኑ ተከተሉኝ ሳይሆን እያንዳንዳችንን በየስማችን እየጠራ ና ተከተለኝ ነው የሚለው። እግዚአብሔር ለሁሉም ለእያንዳንዳችን ጊዜ ያለው፣ እያንዳንዳችን ለይቶ የሚያውቅ ነው። ስለዚህ እንድንከተለው ሲጠራን ጥሪው ማኅበራዊ ሳይሆን ግላዊ ነው፣ እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን ጋር ግኑኝነት በመፍጠር ግላዊው ጥሪ ቤተ ክርስትያናዊ ቅርጽ ያለው ሆኖ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አካል በመሆነቸው ቤተ-ክርስትያን የሚጸና፣ እርሱም በቁምስናዎች እና በክልላዊት ቤተ ክርስትያን ዘንድ የሚንጸባረቅ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ውህደት ባላት ቤተ-ክርስትያን ዘንድ የሚገለጥ እና የሚኖር ጥሪ መሆኑ አብራርተው፣ ይኸንን ክህነታዊ ጥሪ በመኖር ያለፉት አባቶች ካህናት በማሰብ የእያንዳንዱ ካህን ጥሪ ካለፉት አበው ካህናት ጋር እና ገና ይኸንን ጥሪ ለመኖር ከሚጠሩት ጋር ኅብረት ያለው ነው። ዘመን ክልል እና አገር የማያግደው እያንዳንዱ የተጠራ ካህን የሚያዋኅድ በቤተ ክርስትያን ዘንድ የሚያዋህድ ጥሪ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንደ አብነት በመጥቀስ የክርስትያን ሕይወት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚሰጥ ጥሪ እርሱም ናና እይ ከሚለው የጥሪ ቃል የሚጀምር እና እንደ እመቤታችን እና ደቀ መዛሙርት እነሆኝ የሚል ቅድመ ሁኔታ የማይደረድር መልስ የሚሻ ነው። ይኽ ደግሞ እኔን ለምጥራት ወደ እኔ የሚመጣው ታላቅ ሆኖ እያለ የእኔ ጓደኛ በመሆን ስለ እኔ የሚሰቃየው ስለ እኔ ድህነት እራሱ ለሞት አሳልፎ የሚሰጠው እግዚአብሔርን መምሰል የሚጠይቅ የትህትና የአገልግሎት ጥሪ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.