2011-03-04 15:57:52

የካቶሊክ እና የአይሁድ ሃይማኖት የጋራ ኮሚቴ


በፈረንሳይ ርእሰ ከተማ ፓሪስ ዓለም አቀፍ የአይሁድ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው ግኑኝነት በሚከታተለው ድርገት እና የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የዚህ ምክር ቤት ከአይሁድ RealAudioMP3 ሃይማኖት ጋር የሚደረገው ውይይት የሚንከባከበው ድርገት በጋራው አነሳሽነት የተካሄደው ውይይት የጋራው ውይይት የተጀመረበት 40ኛውን ዓመት ለመዘከር እና ባለፉት አርባ ዓመት የተከናወነው የጋራው ግኑኝነት መለስ ብሎ በማስተንተን የጋራው ግኑኝነት ለመጪው የሚከተለውን መንገድ በጋራ ለመቀየስ በሚል እቅድ መሠረት ያካሄዱት 21ኛው ጉባኤ ከትላንትና በስትያ መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ጉባኤው በሌልው ረገድ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ጭምር ርእሰ ጉዳይ በማድረግ መወያየታቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ማንኛውም ለውጥ እና ሥርዓት የውሁዳን ኅብረትሰብ እና ኃይማኖት የሚቀናቀን እና ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆን እንደማይገባው ጉባኤው በጥልቀት እንዳስታወቀ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በጉባኤው ፍጻሜ የካቶሊክ እና የአይሁድ ሃይማኖት የጋራው ድርገት ባወጣው የጋራ መግለጫ፣ በእግዚአብሄር ስም በዓለማችን በሚፈጸመው ዓመጽ በማውገዝ ጸረ ክርስያን ዓመጽ እና ጸረ ሴማዊ አመጽ ጸረ አገረ እስራኤል ተግባሮች ጭምር በመቃወም እና በማውገዝ በእግዚአብሔር ስም የሚፈጸመው ዓመጽ ጸረ እግዚአብሔር መሆኑ በማብራራት፣ የጋራው ድርገት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ሰላማዊ የማኅበራዊ ኑሮ እንዲረጋገጥ አበክሮ እንደሚንቀሳቀስ እና ለዚህ ዓለም የእያንዳንዱ ሃይማኖት ተከታይ እንዲያነጽ እና ሁሉም ለሰላም ባህል እዲታጠቅ ለማገዝ አበክረው እንደሚጥሩ እና በሁለቱ ሃይማኖቶች መካከል ያለው መልካም ግኑኝነት አመርቂ መሆኑ የጉባኤ ፍጻሜ የጋራው ሰነድ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.