2011-03-04 15:54:36

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ ጳጳሳዊ የጸጥታ አስከባሪ የስዊዘርላንድ ዘብ ጠባቂ ኃይል አገልግሎት


ብዙውን ጊዜ በዓለማችን ሰዎች የሚከተሉት የኑሮ ሥልት እና የሚያሰሙት እና የሚከተሉት አስተሳሰብ በውስጣቸው ላለው የሥልጣን ጥማት እና ለገዛ እራሳቸው የግል ጥቅም ለማረጋገጥ በመሻት ላይ የተመሰረተ የተደናገረ ዝናን ሃብት RealAudioMP3 የሚሻ ሥውር የሆነ ምኞች የሚያጎላ ሆኖ እንደሚታይ ነው። ሆኖም ሥልጣን በእግዚአብሔር ዓይን ሲታይ ከፍተኛ አገልግሎት እና ኃላፊነት ነው። በሥነ ቤተ ክርስትያን ቋንቋ ሚኒስትር ሲባል ሥልጣን ሳይሆን አገልግሎት እና የአገልግሎት ኃላፊነት የሚገልጥ መሆኑ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ትላትና ጳጳሳዊ የጸጥታ አስከባሪ የስዊዘርላንድ ዘብ ጠባቂ 12 አዲስ አባላት የዚህ የጳጳሳዊ የጸጥታ ኃይል አባላት እንዲሆኑ በይፋ በተደረገው አቀባበል ምክንያት በግል የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ጸሎት ቤት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ማብራራታቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ኅትመቱ አስታወቀ።

ብፅዕነታቸው ባሰሙት ስብከት፣ የክርስቶስ ተልእኮ ለራስ ክብር እና ዝና ለሚደረገው መራወጥ የሚጻረር ቀዳሜ ለመሆን ትሁት ከፍ ለማለት ዝቅ ብሎ የሁሉም አገልጋይ መሆን እና የቅዱስ ቁርባን አፍቃሪ አክባሪ ተካፋይ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ማክበር ብሎም ለቅድሱ ጴጥሮስ ተከታት ማክበር የሚሉትን ሶስት ነጥቦች መሠረት በማድረግ ጳጳሳዊ የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ተልእኮ በመግለጥ፣ እምነት ተስፋ እና ፍቅር ለሚጠይቀው አገልግሎት መጠመድ እና ክርስቶስን በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ በተሰኘው በቤተ ክርስትያን ተልእኮ መሳተፍ ማለት መሆኑ ማብራራታቸው እና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በማገልገል እና በማፍቀር ቤተ ክርስትያን እና ክርስቶስን ታገለግላላችሁ ታፈቅራላችሁ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ከለላ መሆን ለክርስቶስ ከለላ መሆን ማለት ነው በማለት ያሰሙት ስብከት እንዳጠቃለሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.