2011-03-04 15:59:01

ብፁዕ ካርዲናል ሳራህ በብሩንዲ


የኮር ኡኑም ማለትም ውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ በብሩንዲ ሐዋርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ብፁዕነታቸው የብሩንዲ RealAudioMP3 የዳግመ ግንባታ መርሃ ግብር ለመደገፍ እና ለክልሉ ሕዝብ የቅዱስ አባታችን ቅርበት እና ጸሎት ለማረጋገጥ በሚል እቅድ መሠረት እያካሄዱት ባለው ሐዋርያዊ ጉብኝት መሠረት በብሩንዲ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ጽ/ቤት ከብሩንዲ የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ጋብሪኤል ቲሰዘራና ጋር መወያየታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በብሩንዲ በመከናወን ላይ ባለው የዳግመ ግንባታ እቅድ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ የተልእኮ ዘርፎች ሥር በመሳተፍ ለሰብአዊ መፍነሳዊ የሥነ ምግባር እና የግብረ ገብ እድገት በአገሪቱ እውን እንዲሆን በዚሁ ረገድ አቢይ አገልግሎት እየሰጠች መሆንዋ ብፁዕ ካርዲናል ሳራህ ያሰመኡበት ሐሳብ የብሩንዲ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ቲሰዘራና በማስተጋባታ ቤተ ክርስትያን እየሰጠውችው ያለው የተሟላ እድገት ድጋፍ እንዲቀጥልበት አደራ እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.