2011-03-04 15:56:45

ብፁዕ አቡነ ማሪያ ቸሊ፦ ቤተ ክርስትያን በእደ-ጥበብ የተራቀቀው የዘመኑ ባህል ቋንቋ ተጠቃሚ


የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የጠራው የቤተ ክርስትያን የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ለመደገፍ የወቅቱ በሥነ አኃዝ ሥልጣኔ እና እድገት ላይ የጸናው አዲስ ቋንቋ ተጠቃሚ እንድትሆን እና እውቀቱም ጭምር እንዲኖራት ለመደገፍ የሚል ማእከላዊ ሐሳብ ላይ ያተኮረ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ሲካሄድ የሰነበተው ዓወደ ጥናት ትላትና መጠናቀቁ RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ስለ ተካሄደው ዓወደ ጥናት በማስደገፍ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ተጋባእያኑ እ.ኤ.አ. መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ተቀብለው በሰጡት መሪ ቃል፣ ቤተ ክርስትያን እና አገልጋዮች ለተጠሩበት የአስፍሆተ ወንጌል አላማ ሳያመነቱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እና በቤተ ክርስትያን መሪነት በመቀጠል፣ ሆኖም ተልእኮው ወቅቱ ከሚያረጋግጠው የእደ ጥበብ እድገት ጋር የሚጓዝ እና የወቅቱ በሥነ አኃዝ የተራቀቀው እድገት ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባል እንዳሉ ዘክረው፣ አንድ ቋንቋ ካንድ ባህል ይወለዳል፣ ቋንቋ የባህል መግለጫ ነው ስለዚህ የወንጌል ባህል ለማስፋፋት የዘመኑ ባህል እና እድገት ቀርቦ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ቤተ ክርስትያን በአሁኑ ወቅት ዓለማችን እያቀፈ ያለው የሥነ አኃዝ ባህል መሆኑ በማብራራት፣ የወንጌል ባህል ለማስፋፋት ይኸንን የሥነ አኃዝ ባህል ቀርቦ ማወቅ የውሉደ ክህነት የልኡካነ ወንጌል በጠቅላላ የሁሉም መንፈሳዊ ማኅበራት እና ምእመናን ኃላፊነት ነው ብለዋል።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና ቃሉን በማዳመጥ እና በማስተንተን የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ጸሎት አድርጎ ማቅረብ ወሳኝ ነው። ሆኖም ግን ከዚህ በመቀጠል የሚቀርበው ጸሎት የሚሰጠው ወንጌላዊ አገልግሎት፣ መሠረቱ እና ቋሚ ነገሩን ሳይስት የወቅቱ ባህል የሚያገናዝብ መሆን አለበት። ወደ ሁሉ ዓለም ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ የሚለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥሪ፣ ወደ ሁሉ መሄድ ማለት በምትሄድበት እና አገልግሎት በምትሰጥበት ክልል ያለው ቋንቋ ባህል ማወቅ ወሳኝ ነው። ስለዚህ የሌላው ቋንቋ እና ባህል ለማወቅ ክፍት እና ትሁት በመሆኑ የሁሉም ባህል፣ የባህል ሥልጣኔም ይሁኑ በሥነ አኃዝ የተራቀቀው እድገት ቀርቦ በማወቅ በወንጌል እንዲሰበክ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ያስገነዘበ ዓወደ ጥናት ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.